በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ሁሉም ሰው በሕግ ፊት እኩል የሚሆንበትን ጊዜ ተስፋ አደርጋለሁ" - ከፍያለው ተፈራ


ከፍያለው ተፈራ
ከፍያለው ተፈራ

"የሦስተኛ ዓመት ትምሕርቴን ጨርሼ ወለጋ ቤተሰቦቼንለመጠየቅ መንገድ ጀመርኩ። መስከረም 3/1999ዓ.ም ካደርኩበት አዲስ አበባ ካራ ቆሬ የምትገኝው እህቴ ቤት ወጥቼ ከጓደኞቼ ጋራ ወደ አውቶብስ ተራ መንገድ ጀመርን። አንድ ፌርማታ እንደሄድን ተኩስ ተከፈተብን። ሦስቱ ወዲያው ሞቱ። እኔ አንድ እግሬ ተጎዳ። ፖሊስ ሆስፒታል ገባሁና ጤነኛው እግሬ ተቆረጠ። ሁለቱም ተቆርጦ ከእነ ቁስሎቼ ወደ ማዕከላዊ ተወሰድኩ"- አርብ ዕለት ከእስር የተፈታው ከፍያለው ተፈራ የተናገረው ነው።

"አንድ እግሬ በጣም ተጎድቶ ነበር። አንድ እግሬ ደግሞ ጤነኛ ነበር። የመጀመሪያው እግሬ ታክሞ መዳን ሲገባው እኔን ሳያስፈቅዱና ሳያስፈርሙኝ ጤነኛውን እግሬን ሦስት ጊዜ ቆረጡት። ቆይቶ ደግሞ ግራ እግሬ ተቆረጠ"

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ)

"ሁሉም ሰው በሕግ ፊት እኩል የሚሆንበትን ጊዜ ተስፋ አደርጋለሁ" - ከፍያለው ተፈራ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:11 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG