በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞ የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ሲልቪዮ ቤርሎስኮኒ ዐረፉ


የቀድሞ የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ሲልቪዮ ቤርሉስኮኒ
የቀድሞ የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ሲልቪዮ ቤርሉስኮኒ

የቀድሞ የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ሲልቪዮ ቤርሉስኮኒ፣ በ86 ዓመታቸው ከዚህ ዓለት በሞት ተለዩ።

ሉኪሚያ በተሰኘው የደም ካንሰር የተያዙት ቤርሉስኮኒ፣ በዚኽ ወር፣ ለሁለተኛ ጊዜ ዐርብ ዕለት፣ ሆስፒታል ገብተው ነበር። ባለፉት ዓመታት፥ በልብ ሕመም፣ በፕሮስቴት ዕጢ ካንሰር ሲሠቃዩ የቆዩት ቤርሎስኮኒ፣ ከሦስት ዓመታት በፊትም፣ በኮሮና ቫይረስ ተይዘው ሆስፒታል ገብተው ነበር።

የቢሊየኔሩ የሚዲያ ሞጋች ቤርሉስኮኒ የቀብር ሥነ ሥርዐታቸው፣ ከነገ በስቲያ ረቡዕ በመኖሪያቸው ሚላን አቅራቢያ፣ በብሔራዊ ደረጃ እንደሚከናወን ተመልክቷል፡፡

ስለ ቤርሉስኮኒ ሞት፣ ልዩ ልዩ የዓለም መሪዎች አስተያየታቸው የሰጡ ሲኾን፣ ከእነርሱም፣ በዩክሬኑ ጦርነት የደገፏቸው የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እንደሚገኙበት ተነግሯል፡፡

ፑቲን፣ “እውነተኛ ወዳጅ” ያሏቸው ቤርሉስኮኒ፣ ሞታቸውን፥ “የማይጠገን ኅልፈት” ብለውታል፡፡

ቤርሎስኮኒ፣ የጣልያንን ፖለቲካ እና ባህል የቀየሩ፣ የተመሠረቱባቸውን በርካታ ክሦች እና የወሲብ ቅሌቶች የተከላከሉ እንደነበሩም ተነግሮላቸዋል፡፡

XS
SM
MD
LG