በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና ረፍት:- የቀድሞው የግብፅ ፕሬዚዳንት ሞሃመድ ሙርሲ አረፉ


ፎቶ ፋይል:- ሞሃመድ ሙርሲ
ፎቶ ፋይል:- ሞሃመድ ሙርሲ

የቀድሞው የግብፅ ፕሬዚዳንት ሞሃመድ ሙርሲ በዛሬው ዕለት ማረፋቸውን የመንግሥቱ ቴሌቭዢን አስታወቀ።

በዜናው መሰረት የሥድሳ ሰባት ዓመቱ ሙርሲ ህይወታቸው ያለፈው በመንግሥታዊ ሥለላ ወንጀል ክስ ፍርድ ቤት ችሎት ላይ ቀርበው ራሳቸውን ከሳቱ በኋላ ነው። ሆስፒታል ሳይደርሱ በፊት ህይወታቸው ማለፉን ነው ዜናው የገለፀው።

በሙስሊም ወንድማማቾች ቡድን ውስጥ ከፍተኛ የመሪነት ቦታ የነበራቸው ሞሃመድ ሙርሲ እኤአ በ2013 በአስተዳደራቸው ላይ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ የጦር ሰራዊቱ ከሥልጣን እንዳስወገዳቸው ይታወሳል።

ከዚያም በቀደመው ዓመት በፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ለመወዳደር ባስገቡት የዕጩነት ማመልከቻ ዋሽተዋል ተብሎ በቀረባበቸው ክስ የሰባት ዓመት እስራት ተፍርዶባቸው ከዚያ በኋላ የመንግሥታዊ ሥለላ ወንጀል ክስ ተከፍቶባቸዋል።

ሂዩማን ራይጽ ዋች ክሱን በፖለቲካ የተነሳሳ ብሎታል። ሞርሲ እጅግ ጭካኔ በተመላበት እና ኢሰብዓዊ በሆነ አያያዝ ቤተሰብ እንዲጎበኛቸውም ሆነ የህክምና ዕርዳታ እንዳያገኙ ተደርጎዋል ሲሉ የሰብዓዊ መብት ድርጅቱ የመካከለኛው ምስራቅ ዋና ዳይሬክተር ሳራ ሊያ ዊትሰን ዛሬ በትዊተር ፅፈዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG