በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፖብሊክ ባለሥልጣን የጦር ወንጀል ክስ ቀረበበት


ፎቶ ፋይል፡-ፓትሪስ ኤድዋርድ ኛሦና
ፎቶ ፋይል፡-ፓትሪስ ኤድዋርድ ኛሦና

አንድ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፖብሊክ ከፍተኛ የእግር ኳስ ባለሥልጣን የጦር ወንጀል ክስ ቀርቦበት ፈረንሳይ ውስጥ ተይዞ ታሥሯል።

አንድ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፖብሊክ ከፍተኛ የእግር ኳስ ባለሥልጣን የጦር ወንጀል ክስ ቀርቦበት ፈረንሳይ ውስጥ ተይዞ ታሥሯል።

ፓትሪስ ኤድዋርድ ኛሦና ቀድሞ የፀረ ባላካ ሚሊሽያ ብሄራው ጠቅላላ አስተባባሪ እንደነበር፤ የዓለምቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ጠበቆች ተናግረዋል።

አብዛኞቹ ክርስቲያኖች የሆኑት ሚሊሽያዎች መሪ የነበረው ኛሦና፣ በጦር እና በሰብዓዊ ወንጀሎች እንዲሁም በግድያ፣ በዘር ማጥፋት፣ ከሃገር በማባረር፣ በጭቆና፣ ሲቪሎችን በማጥቃት፣ ሰቆቃ በመፈፀምና ሕጻናትን ለውትድርና በመመልመል ይከሰሳል።

የፀረ ባላካ ሚሊሽያ እአአ በ2013 የተመሠረተው የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፖብሊክን ዋና ከተማ ባንጉይን ተቆጣጥረው - ፕሬዚዳንቱን ፍራንሷ ቦዚዜን ከሥልጣን ያባረሩትን እስላማዊ የሴሌካ ሽምቅ ተዋጊዎች በመቃወም እንደነበር ይታወሳል።

እአአ በ2014 ኛሦናና ሌሎች 19 የጦር ወንጀለኞች እንዲታሠሩ ጥሪ ያቀረበው አምነስቲ ኢንተርናሽናል የኛሦና በቁጥጥር ሥር መዋል በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፖብሊክ ተጠያቂነት እንዲኖር ለተያዘው ትግል ትክክለኛ ዕርምጃ ነው ሲል አወድሶታል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG