በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በግዳጅ የማጭበርበር ሥራ እንዲሠሩ ተሰማርተው የቆዩ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከሚያንማር ድንበር አቅራቢያ በእስር ላይ ናቸው


በግዳጅ የማጭበርበር ሥራ እንዲሠሩ ተሰማርተው የቆዩ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ሰዎች
በግዳጅ የማጭበርበር ሥራ እንዲሠሩ ተሰማርተው የቆዩ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ሰዎች

ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የመጡ እና ማጭበርበር ሥራዎችን እንዲሠሩ በግዳጅ የተሰማሩ፣ ቁጥራቸው በሺሕዎች የሚገመት፤ በጽኑ የተዳከሙ፣ የታመሙ እና በድንጋጤ የተዋጡ ወጣት ወንዶች እና ሴቶች፣ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎች አጥልቀው አንዳንዶቹም ዐይኖቻቸውን ጭምር ሸፍነው፤ እፍንፍን ባለ ሁኔታ ውስጥ ሚያንማር ድንበር አቅራቢያ እስር ላይ መኾናቸው ተገለጸ።

የአንዳንድ አሜሪካውያንን እና የሌሎችን የቁጠባ ገንዘብ ለማጭበርበር በኃይል ተገደው ተሰማርተውበት ከነበረው ሥራ እንዲለቀቁ ከተደረገ ሳምንታት በኋላ አሁንም ሚያንማር ውስጥ ኾነው ወደ የአገሮቻቸው ለመመለስ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የሚገኙበት ሁኔታ የተፋፈገ፤ ለተለያዩ በሽታዎች የሚያጋልጥ፤ ምንም ዓይነት የሕክምና አገልግሎት የማያገኙበት፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በጋራ ለመጠቀም የተገደዱባቸው ጥቂት የመጸዳጃ ቤቶች ያሉበት እና በእጅጉ አሳሳቢ መሆኑን በመጥቀስ ቅሬታቸውን ገልጠዋል።

የዜና ዘገባዎች አክለው እንዳመለከቱት፤ ሰዎቹ በኃይል ተገደው በአካባቢው ተመሳሳይ ሥራዎችን እንዲሰሩ ከተደረጉ ቁጥራቸው 300 ሹሕ እንደሚጠጋ ከሚገመቱ ሰዎች በጣም ጥቂቱ ብቻ ሲኾኑ፤ የተባሉት የማጭበርበር ድርጊቶችም ያከትማሉ ተብሎ አይጠበቅም ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG