በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቻይናና አፍሪካ ጉባዔ


የምዕራብ አፍሪካ ሀገሮች መሪዎች በሚቀጥለው ሳምንት ቤጅንግ ላይ በሚካሄደው የቻይናና አፍሪካ ጉባዔ ላይ ሲሳተፉ የብዙ ሚሊዮንና የብዙ ቢሊዮን ዶላር ውሎች እንደሚፈራረሙ ተገልጿል።

የምዕራብ አፍሪካ ሀገሮች መሪዎች በሚቀጥለው ሳምንት ቤጅንግ ላይ በሚካሄደው የቻይናና አፍሪካ ጉባዔ ላይ ሲሳተፉ የብዙ ሚሊዮንና የብዙ ቢሊዮን ዶላር ውሎች እንደሚፈራረሙ ተገልጿል። ከቻይና ጋር የሚደረጉት ሥምምነቶች ለመሰረተ ልማት ለንግድና ለሌሎችም የልማት ፕሮጀክቶች የሚውሉ መሆናቸው ነው የተጠቀሰው።

ቻይና እስካሁን ለአፍሪካ ሀገሮች ከአንድ መቶ አርባ ሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ ብድር መስጠቷ ሲታወቅ፣ የዘንድሮው ጉባዔ ላይ ደግሞ የገንዘብ ነክ ግንኙነቶቻቸውን ይበልጡን የሚጠናክር እንደሚሆን ይጠበቃል።

የዩናይትድ ስቴትስ የፖለቲካ ሰዎች በበኩላቸው በቻይና ብድር ላይ ከመጠን በላይ መተማመን አሳሳቢ መሆኑን እያመለከቱ ናቸው። የቻይናን እና የአፍሪካን ግንኙነቶች የሚያጠኑ ተንታኞች የአፍሪካ መሪዎች የሀገሮቻቸውን ጥቅሞች በተሻለ የሚያስከብሩ ሥምምነቶች ላይ ለመደራደር ዕድል እንዳላቸው ይገልጻሉ፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG