በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የምግብ ዋስትና - የዓለም ደኅንነት


ዶ/ር ገቢሣ ኢጀታ
ዶ/ር ገቢሣ ኢጀታ

የምግብ ዋስትናን በዓለም ዙሪያ ማረጋገጥ የዩናይትድ ስቴትስ ጥቅም ጉዳይ መሆኑ ላለፉት ሁለት ቀናት መጋቢት 20 እና መጋቢት 21 / 2009 ዓ.ም. ዋሺንግተን ዲሲ ላይ በተካሄደው ዓመታዊው የዓለም የምግብ ዋስትና ጉባዔ ላይ ተገልጿል፡፡

የምግብ ዋስትናን በዓለም ዙሪያ ማረጋገጥ የዩናይትድ ስቴትስ ጥቅም ጉዳይ መሆኑ ላለፉት ሁለት ቀናት መጋቢት 20 እና መጋቢት 21 / 2009 ዓ.ም. ዋሺንግተን ዲሲ ላይ በተካሄደው ዓመታዊው የዓለም የምግብ ዋስትና ጉባዔ ላይ ተገልጿል፡፡

የዓለማችንን እያሻቀበ የመጣ የምግብ ፍላጎት ማርካት የሚቻለው ከእንግዲህ በወረት ብዛትና በመዋዕለ ነዋይ ፍሰት ብቻ አይደለም፤ መክፈል መቻልም ብቻውን የምግብ ዋስትናን አያመጣም፡፡ ከእንግዳህ እህል እንዲትረፈረፍ የሚሻ ቢኖር ሙሉ አቅምና ጥሪቱን ተሰጥዖና ችሎታ ያለው፤ በቂ መሣሪያና ዕውቀት የታጠቀ የሰው ኃይል መገንባት ላይ ያፍስስ - ይህ የዘንድሮው ቺካጎ ካውንስል የሚባለው በዓለማችን አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ ንግግሮችን የሚያበረታታው ተቋም የሚያዘጋጀው የዓለም የምግብ ዋስትና ጉባዔ ትኩረት ነው፡፡

በዚህ መስክ የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ ተመሣጥረውና ተጋግዘው መሥራታቸው ብቻ ነው የሰው ኃብትን ማልማትና ማጨድ፣ እንዲሁም ወደ አዲስ ዓይነት ሽግግር መውሰድ የሚያስችለው፡፡

በሲምፖዚየሙ ላይ የተሣትፉትና ፅሁፍም ያቀረቡት የፐርዱ ዩኒቨርሲቲው የግብርና ዲፓርትመንት ፕሮፌሰርና በአውሮፓ የዘመን አቆጣጠር የ2009 ዓ.ም. የዓለም የምግብ ሽልማት አሸናፊው ዶ/ር ገቢሣ ኢጀታ በተለይ የአፍሪካን ግብርና እየተፈታተኑ፣ ምርቱንም ወደኋላ እየጎተቱ ያሉ የተፈጥሮ አካባቢና የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳዮች የተደጋገሙ የኤል ኒኞ ክስተቶች፣ የአፍሪካ ግብርና በቂየዕውቀት ሽግግርና ዘመናዊ ትጥቅ በበቂ ሁኔታ አለማግኘቱ፣ ተቋማት በሚገባው መጠን የተጠናከሩ አለመሆናቸው መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የምግብ ዋስትና - የዓለም ደኅንነት
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:18 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG