በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መረጃ የማግኘት ነፃነት ሕግ


ይህ የሚጠናቀቀው የአውሮፓዊያኑ ጁላይ ወይም ወርኃ ሐምሌ በዩናይትድ ስቴትስ “ፍሪደም ኦፍ ኢንፎርሜሽን አክት” ማለትም መረጃ የማግኘት ነፃነት ሕግ ሥራ ላይ የዋለበት ሃምሣኛ ዓመት ነው።

ይህ የሚጠናቀቀው የአውሮፓዊያኑ ጁላይ ወይም ወርኃ ሐምሌ በዩናይትድ ስቴትስ “ፍሪደም ኦፍ ኢንፎርሜሽን አክት” ማለትም መረጃ የማግኘት ነፃነት ሕግ ሥራ ላይ የዋለበት ሃምሣኛ ዓመት ነው።

ሕጉ የመንግሥት አሠራር ግልፅ እንዲሆን ቃል የሚገባና ከዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት መረጃ ለማግኘት ለሚጠይቅ ማንም ሰው እንዲለቀቅለት የሚያዝ ሥር-ነቀል ፅንሰ ሃሳብ ያለው ሕግ ነው፡፡

ከመንግሥት መረጃ የማግኘት መብት ሊነፈግ የሚችለው ከግል ገመና እና ከብሔራዊ ፀጥታ ጋር የተያያዘ ከሆነ ብቻ ነው፡፡ ከእነዚህ ውጭ የሆኑ የመንግሥት መረጃዎችን ግለሰብ ከጠየቀ ሊለቀቁለት ይገባል ነው የሚለው መረጃን የማግኘት ነፃነት ሕጉ፡፡

በዩናይትድ ስቴትስ መረጃ የማግኘት ነፃነት ለጋዜጠኞች በጣም ጠቃሚ ሕግ ነው፡፡ ምንም እንኳ ጋዜጠኞች መረጃ ከመንግሥት ለመጠየቅ ይህን ሕግ የሚጠቀሙት ከአሥር ከመቶ ያነሰ ጊዜ ቢሆንም ሕዝቡ ስለሚያስተዳድረው መንግሥት እንዲያውቅ በማስቻል ሕጉ ከፍተኛ ጫና ፈጥሯል።

ሪፖርተራችን አራዲታ ዱኔላሪ ያጠናቀረችውን ትዝታ በላቸው ታቀርባለች፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

መረጃ የማግኘት ነፃነት ሕግ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:50 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG