በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፍሎሪዳ ት/ቤት ለ17 ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው ትናንት ፍ/ቤት ቀረበ


APTOPIX School Shooting Florida
APTOPIX School Shooting Florida

በአንድ የፍሎሪዳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ተኩስ ከፍቶ፣ እስካሁን በታወቀው አኃዝ መሠረት፣ ለ17 ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው ግለሰብ፣ ትናንት ሐሙስ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርቦ፣ ያለ ዋስ መብት በእስር እንዲቆይ ተወስኖበታል።

በአንድ የፍሎሪዳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ተኩስ ከፍቶ፣ እስካሁን በታወቀው አኃዝ መሠረት፣ ለ17 ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው ግለሰብ፣ ትናንት ሐሙስ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርቦ፣ ያለ ዋስ መብት በእስር እንዲቆይ ተወስኖበታል።

በ17 ወንጀሎች የተከሰሰው ኒኮላስ ክሩስ እስከሚቀጥለው ችሎት ያለ ዋስ መብት በእስር እንዲቆይ ሲወሰንበትና፣ ዳኛ ኪም ቴራስ ሞሊካም ነፍሰ ገዳዩን ክሩዝ በከፍተኛ ወንጀሎች ነው የተከሰስከው ሲሉት ጠበቃው ተቃውሞ እንዳላቀረበም ተስተውሏል።

14 ተማሪዎችና 3 መምህራን የሚገኙበት የ17ም ሰለባዎች ማንነት በአሁኑ ሰዓት ታውቋል።

የታወከ እና የተረበሸ ባሕሪ ያለው መሆኑ የተገለጸው የ19 ዓመቱ ወጣት ኒኮላስ ክሩዝ ባለፈው ዓመት በምግባረ ብልሹነት እስከተባረረ ድረስ፣ ከማያሚ በስተሰሜን 70 ኪሎ ሜትር ላይ ፓርክላንድ ውስጥ በሚገኘው የዳግላስ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ እንደነበርም ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በብዙ መቶዎች የሚቆጠር ሕዝብ ትናንት ማታ ለሟቾች ኃዘኑን ለመግለጽ ተሰባስቦ እንደነበና በፀሎትም የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓት ማካሄዱ ታውቋል።

በሌሎች የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች፣ ለምሳሌ በካሊፎርኒያ፣ በላስ ቬጋዝ፣ በቴክሳስና በኬንታኪም እንደተካሄደ ተገልጧል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG