በዩናይትድ ስቴትሷ የካሊፎርኒያ ክፍለ ግዛት ትናንት እሁድ በድጋሚ የተከሰተውን ከባድ የአየር ሁኔታ ተከትሎ አንዳንድ አካባቢዎች በከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ተጥለቅልቀዋል፡፡
ከ355, 000 በላይ የሚሆኑ የክፍለ ግዛቲቱ ነዋሪዎች የመብራት አገልግሎት መቆራረጥ የገጠማቸው ሲሆን፤ በአካባቢው እምብዛም ያለተለመደ የከባድ ዝናብና አውሎ ነፋስ ማስጠቀቂያም ደርሷቸዋል፡፡
የሳን ፍራንሲስኮ የባህር ወሽመጥ አካባቢ በኃይለኛ አውሎ ንፋስ በመመታቱ የወደቁ ዛፎች የኤሌክትሪክ መስመሮችን ጨምሮ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል፡፡
በአንዳንድ አካባቢዎች በሰዓት ከ60 ማይል ወይም በሰዓት ከ128 ኪሎ ሜትሮች ፍጥነት የሚጓዝ እውሎ ነፋስ መዘገቡ ሲነገር በተራራማ ካባቢዎች ላይ በሰዓት 80 ማይሎች ወይም 128 ኪሎ ሜትሮች ፍጥነት ሲጓዝ ተመዝግቧል፡፡
በደቡባዊ ካሊፎርኒያ በቅርቡ በሰደድ እሳት በተጠቁ አካባቢዎች ሌላ የጎርፍ እና የአፈር መንሸራተት አደጋ ሊደርስ ይችላል የሚል ስጋት በመኖሩ፣ ነዋሪዎች አካባቢዎቹን ለቀው እንዲወጡ ባለሥልጣናት አስጠንቅቀዋል፡፡
መድረክ / ፎረም