በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"በቀላሉ ቢገደብ ኖሮ እርሻችንን በጎርፍ አናጣም ነበር" የመቂ ገበሬዎች


ኤል ኒኞ በአፍሪካ ቀንድ ያስከተለው ድርቅና ጎርፍ /ፎቶ ሮይተርስ/
ኤል ኒኞ በአፍሪካ ቀንድ ያስከተለው ድርቅና ጎርፍ /ፎቶ ሮይተርስ/

ከአዲስ አበባ 131 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው መቂ አካባቢ ባሉ እርሻ ቦታዎች ቦታውን ስቶ የገባ ጎርፍ እርሻቸውን በሙሉ ከጥቅም ውጭ እንዳደረገባቸው የአካባቢው ገበሬዎች ይናገራሉ። እንዲህ ያለ የጎርፍ አደጋ ቀድም ብሎ ተከስቶ ያውቅ ስለነበረም ቦታው በአፈር እንዲገደብ አስቀድመው ጠይቀው ሰሚ አለማግኘታቸውን ይገልፃሉ። የአካባቢው አስተዳደድር በተፈጥሮ የመጣ ስለኾነ ምንም ማድረግ አይቻልም ይላል።

በእርሻ ሥራ በተለይ አትክልትና ፍራፍሬ አምራችነት የሚታወቀው “መቂ” ከተማና አካባቢዋ ባሉ የእርሻ ቦታዎች በእርሻ ሥራ ላይ የተሠማሩ ገበሬዎች ሰሞኑን እየዘነበ ባለው ዝናብ ከሌላ ቦታ አቋርጦ የሚመጣ ወንዝ መንገድ ሰብሮ ወደ እነርሱ የእረሻ ሥራ እየገባ ያመረቱትን ምርት በሙሉ ይዞባቸው እንደሄደ ተናገሩ።

የቤተሰብ አስተዳዳሪ መኾናቸውን የሚገልጹት በመቂ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ሮባ ኮርጂ በመቂ ግሪታ በተባለ ቦታ በእርሻ ቦታቸው ላይ አደጋው በተደጋጋሚ የሚደርስ በመሆኑ በአፈር ግድብ እንዲሠራላቸው አስተዳሩን ጠይቀው ባለመሠራቱ የሰሞኑ ዝናብ እርሻቸውን እንዳጠፋባቸው ይናገራሉ።ገንዘቡን በብድር ሲወስዱ ውጤታማ ሥራ ሠርተው ቤተሰቦቻቸውን ለመለወጥ በማሰብ እንደኾነ የሚናገሩት አቶ ሮባ አፈሩ በቀላሉ ተሞልቶ ቢገደብ ኖሮ እርሳቸውን ጨምሮ ሌሎች ገበሬዎችም ለኪሳራ ሊጋለጡ አይችሉ እንደነበር ይናገራሉ።

በዛው አካባቢ ነዋሪ እንደኾነና በግብርና ሥራ እንደሚተዳደር የገለጸልን አቶ ካሳዬ ነጎ እርሱም የቤተሰብ አስተዳዳሪ መኾኑን ገለጾ ወደ 147 ሺሕ ብር ወጪ ያወጣበት እርሻ ተጠራረጎ እንደተወሰደበት ይናገራል። እዛ ቦታ ላይ ከ100 በላይ ገበሬ እርሻ መውደሙንም ይናገራል።ገበሬዎቹ ያነሱትን ቅሬታ ይዤ የመቂ ከተማ አስተዳደር ምክትል ኃላፊ አቶ ቦንሳ አነጋግሬ ነበር። አደጋው በተፈጥሮ የመጣና በከፍተኛ የወሃ ሙሌት ድንገት የተፈጠረ እንደኾነ ተናግረዋል።

ገበሬዎቹ እስካሁን የደረሰው አደጋ እንዳለፈና ከዚህ በኋላ ላለው ጥበቃ እንዲደረግላቸው፣ ቢያንስ የዘር መግዣ ዕርዳታ እንኳን እንዲሰጣቸው መጠየቃቸውን ገልፀን ቦታውን በአፈር ገድቦ መከላከል ከተቻለ ለምንስ እንዳልተደረገ ጠቀሰን ላነሳንላቸው ጥያቄ ምላሽ ሳይሰጡን ስልኩ ተቋርጧል።

XS
SM
MD
LG