በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ ክልል በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ከ28ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል


ፎቶ ፋይል፦ ሀዋሳ
ፎቶ ፋይል፦ ሀዋሳ

በደቡብ ክልል ባለፉት አሥር ዓመታት ያልተመዘገቡ የተፈጥሮ አደጋዎች እየተፈጠሩ በ10ሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ለስቃይ እያጋለጠ መሆኑን የደቡብ ክልል የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

በአንድ ወር ብቻ ከ28ሺህ በላይ ሰዎች በጎርፍና በናዳ አደጋዎች ከቤታቸውና ቀያቸው የተፍናቀሉ ሲሆን ጥቂት የማይባሉ ሰዎችም መሞታቸውን ገልጠው በቅርቡ በደቡብ ኦሞ ዳሰነች ወረዳ የተፈናቀሉትን የመደገፍ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ተነግሯል።

በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግና መልሶ ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ፈታኝ ማድረጉንም የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ጋንታ ጋሩማ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

በአንፃሩ ግን ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት በጥናት የተደገፈ ተግባር በመከናወን ላይ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በደቡብ ክልል በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ከ28ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:50 0:00


XS
SM
MD
LG