በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ በ5 አመታት ከተረጂነት ለመውጣት የሚያስችሏት የልማት መሰረቶች አልተጣሉም ሲሉ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ገለጹ


ጌታቸው በጋሻው፡ የኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር
ጌታቸው በጋሻው፡ የኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በጥቅምት ወር አዲስ መንግስት ይመሰርታሉ። አመራሩን በአጠቃላይ በአዲስ ትውልድ እንደሚተኩ ያስታወቁት አቶ መለስ ለዚህ አዲስ ትውልድ አዲስና እስካሁን እውን መሆን ያልተቻለ ፈተና አስቀምጠውለታል።

የአምስቱ አመት የኢኮኖሚ ልማት ትራንፎርሜሽን እቅድ ተብሎ የሚጠራ ሰነድ አዘጋጅተው ለመጭው አመራር ከፍ ያለ የእድገት ጣራ አብጅተዋል።

አቶ መለስ አሳባቸውና ግባቸው ኢትዮጵያ የመካከለኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች የሚኖሩባት አገር ሆና ማየት በመሆኑ፣ ለሚቀርቡ ትችቶች ቦታ እንደማይሰጡና አስተዳደራቸው እጂጌውን ጠቅልሎ ወደ ስራ እንደሚገባ ይናገራሉ።

በአምስቱ አመት የልማት መርኃ ግብር ዙሪያ ለመወያየት ሁለት እንግዶችን ለውይይት ጋብዘናል። ዶ/ር ጌታቸው በጋሻው በሀርፐር ዩኒቨርስቲ የኢኮኖሚክስ መምህር ናቸው።

ዶር አክሎግ ቢራራ በአለም ባንክ ከ30 አመታት በላይ በከፍተኛ አማካሪነት የሰሩና በኢትዮጵያ ድህነትን ለማጥፋት የሚቻልበትን መንገድ የሚያመላክት “Waves: Ethiopia’s Endemic Poverty that Globalization Won’t Tackle, but Ethiopians Can” የሚል መጸሃፍ ለንባብ ያበቁ ናቸው።

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG