በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቱኒዚያ ባህር ዳርቻ ጀልባ ሰምጦ ፍልሰተኞች ሞቱ


ፎቶ ፋይል፦ የአፍሪካ ፍልሰተኞች ወደ አውሮፖ ለመሻገር በጀልባ ተሳፍረው፣ ባህር ሲያቋርጡ፤ 10/4/2022
ፎቶ ፋይል፦ የአፍሪካ ፍልሰተኞች ወደ አውሮፖ ለመሻገር በጀልባ ተሳፍረው፣ ባህር ሲያቋርጡ፤ 10/4/2022

በቱኒዚያ ባህር ዳርቻ ፍልሰተኞችን የያዘ ጀልባ ሰጥሞ 5 ሲሞቱ 28 የደረሱበት አልታወቀም ተብሏል፡፡

የአደጋ ግዜ ሠራተኞች 5 አስከሬን ሲያወጡ፣ አምስት ሰዎችን ማዳን ችለዋል። 28 ፍለሰተኞችን ግን ማግኘት አልቻሉም።

የመብት ተሟጋች ቡድኖች ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል እንደገለጹት ጀልባው ሊሰምጥ የቻለው ከልክ በላይ በመጫኑ ነው። ጀልባው 38 ፍልሰተኞችን ጭኖ የነበረ ሲሆን፣ አብዛኞቹ ከአይቮሪ ኮስት መሆናቸው ተገልጿል።

ፍልሰተኞቹ ወደ አውሮፓ ለመሻገር የጣሊያን ደሴት ወደሆነችው ላምፔዱሳ በማምራት ላይ ነበሩ ተብሏል።

በዓለም አደገኛው የፍልሰተኞች የጉዞ መሥመር እንደሆነ በሚነገርለት ማዕከላዊ ሜዲትሬኒያን ባህር አደጋ እየበረከተ መጥቷል።

12 ሚሊዮን ሕዝብ ባላት ቱኒዚያ 21 ሺህ ስደተኞ ይገኛሉ። ፕሬዚዳንቷ ካይስ ሳኢድ ከሰሃራ ግርጌ ካሉ አገራት የሚመጡ ስደተኞች አገሪቱ ውስጥ ወንጀልን አስፋፍተዋል፣ ቱኒዚያ ላይም አሲረዋል በማለታቸው ዘረኛ አስተሳሰብ ነው በሚል ከፍተኛ ውግዘት ገጥሟቸዋል፡፡

የፕሬዚዳንቱን ንግግር ተከትሎ አከራዮች ጥቁር አፍሪካውያኑን ሲያስወጡ በጎዳና ላይ ለመኖር ተገደዋል። በእነርሱ ላይ የሚፈጸመው ወንጀልም በርክቷል።

XS
SM
MD
LG