በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በማዕከላዊ በሶማሊያ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት አምስት ሰዎች ሞቱ


የሶማሊያ ካርታ
የሶማሊያ ካርታ

በማዕከላዊ ሶማሊያ በአንድ ገበያ አቅራቢያ በመኪና ላይ በተጠመደ ቦምብ ትናንት በተፈጸመ ጥቃት 5 ሲቪሎች ሲሞቱ፣ 13 የሚሆኑ ደግሞ መጎዳታቸው ታውቋል።

ከአል ሻባብ ጋር በሚያደርገው ፍልሚያ ችግር እንደገጠመው የሶማሊያ መንግስት ባስታወቀ በሳምንቱ ለተፈጸመው ጥቃት ወዲያውኑ ኃላፊነቱን የወሰደ አካል የለም።

ከአል ቃይዳ ጋር ግንኙነት ያለው አል ሻባብ፣ በሶማሊያ ማዕከላዊ መንግስት ላይ ላለፉት 15 ዓመታት ጥቃት ሲሰነዝር ቆይቷል።

ባለፈው ቅዳሜ በተመሳሳይ በተፈጸመ በመኪና ላይ በተጠመደ ቦምብ ጥቃት 21 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

ዛሬ ሐሙስ ፕሬዝደንቱ በሚገኙበት ማዕከላዊ ሶማሊያ ሊፈጸሙ የነበሩ ሁለት በመኪና ላይ የተጠመዱ ቦምቦች ጥቃት ማክሸፉን የሀገሪቱ የጸጥታ ኃይል አስታውቋል።

በአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል ሞቃዲሹን እንዲለቅ የተገደደው አል ሻባብ፣ አሁንም ሰፊ ገጠርማ አካባቢዎችን በመቆጣጠር ላይ ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG