በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ አፍሪካ በቀጠለው የታክሲዎች አድማ አምስት ሰዎች ተገደሉ

በደቡብ አፍሪካ ኬፕ ታውን ከተማ፣ ባለፈው ሳምንት የጀመረው የሚኒ ባስ ታክሲ ሹፌሮች የሥራ ማቆም አድማ፣ ወደ ሁከት ተለውጦ አምስት ሰዎች መሞታቸውን ባለሥልጣናት ትናንት ማክሰኞ አስታወቁ፡፡.

የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ የታክሲ ካውንስል (ሳንታኮ) ኬፕ ታውን ውስጥ ከአካባቢው አስተዳደር ጋር ተነጋግሮ የተለያዩ ችግሮችን መፍታት ባለመቻሉ ለአንድ ሳምንት በግዛቱ የታክሲ አገልግሎት ዝግ መሆኑን አስታውቋል።

ቅሬታው የተነሳው አዲሱ የማዘጋጃ ቤት ህግ ያለመንጃ ፍቃድ ወይም የመመዝገቢያ ሰሌዳን ማሸከርከር የመሳሰሉት ጥሰቶችን የመቅጣት ሥልጣን ለአካባቢ ባለስልጣናት ከሰጠ በኋላ ነው።

ሁከቱ የተነሳው ባለፈው ሳምንት በተለያዩ የከተማው ክፍሎች ፖሊስ ተሽከርካሪዎችን ይዞ መቅጣት ከጀመረ በኋላ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ከሟቾች መካከል ባላፈው ሀሙስ በተተኮሰ ጥይት የተገደለው የእንግሊዝ ዜግነት ያለው የ40 ዓመት ሰው እንደሚገኝበት የደቡብ አፍሪካ የፖሊስ ሚኒስትር ብሄኪ ሴሌ ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል፡፡

ግድያውና ሁከቱ እየተጣራ መሆኑንም ሚኒስትሩ አክለው ገልጸዋል፡፡

በወደመው ውድመት ዝርፊያና ህዝባዊ አመጽ የተጠረጠሩ 120 ሰዎች ካለፈው ሀሙስ ጀምሮ መታሰራቸውንም ሴሌ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

የኬፕታውን ከተማ ጽህፈት ቤት የስራ ማቆም አድማው ወደ ሥራ በሚሄዱ ሰዎች ላይ ከፍተኛ መጉላላት ያደረሰ ሲሆን፣ አንዳንዴም በህዝብ ማመላለሻ አገልግሎት ላይ በሚደርስ ጥቃት ለችግር ተዳርገዋል ብሏል።

ሳንታኮ ራሱን ከሁከቱ ያገለለ ሲሆን፣ ድርጊቱ የተፈጸመው በአባላቱ ሳይሆን በተቃዋሚዎች ነው ማለቱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG