በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጋዛ ላይ አንድ የመንግሥታቱ ድርጅት የጸጥታ ጉዳይ ሰራተኛ ተገደሉ


ፎቶ ፋይል፡ አብዛኛው የጋዛ ህዝብ ተፈናቅሎ በራፋ እና አካባቢው ይኖራል፣ ጋዛ እአአ መጋቢት 2/2024
ፎቶ ፋይል፡ አብዛኛው የጋዛ ህዝብ ተፈናቅሎ በራፋ እና አካባቢው ይኖራል፣ ጋዛ እአአ መጋቢት 2/2024

ራፋ ወደሚገኘው የአውሮፓ ሆስፒታል በመጓዝ ላይ የነበሩ አንድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የደህንነት እና የጸጥታ ጉዳዮች ሰራተኛ በተሳፈሩበት ተሽከርካሪ ላይ በተከፈተ ጥቃት በመገደላቸው እና አንድ ሌላ የሥራ ባልደረባቸው በመቁሰላቸው የድርጅቱ ዋና ጸሃፊ ክፉኛ ማዘናቸውን ቃል አቀባያቸው ተናገሩ።

የመንግሥታቱ ድርጅት ቃል አቀባይ አያይዘውም ዋና ጸሃፊው በድርጅቱ ሰራተኞች ላይ የሚደርሱትን ማናቸውም ጥቃቶች ማውገዛቸውን እና ሙሉ ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ ማቅረባቸውን አስታውቀዋል። በተጨማሪም በጋዛ የቀጠለው ውጊያ በሲቪሎች ላይ ብቻ ሳይሆን በረድኤት ሰራተኞች ላይ ጭምር ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ በመምጣቱ አስቸኳይ የሰብአዊ ተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ እና ታጋቾች በሙሉ እንዲለቀቁ የሚለውን ጥሪያቸውን ዋና ጸሃፊው በድጋሚ ማሰማታቸውን አመልክተዋል።

እስራኤል ራፋ ውስጥ በሰላማዊ ሰዎችን ከአደጋ መከላከል የሚያስችልም ሆነ፣ የጋዛው ጦርነት ሲያበቃ ሊፈጠር ስለሚችለው ሁኔታ አሳማኝ እቅድ መንደፏን ዋሽንግተን እስካሁን አላየችም"

ሃማስ የሚቆጣጠረው የጋዛ መገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ቢሮ በበኩሉ፣ "የእስራኤል ጦር ደቡባዊ ጋዛ፣ ራፋ ከተማ ላይ አንድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰራተኛ ሲገድል፣ አንድ ሌላ ደግሞ አቁስሏል" ሲል ዘግቧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እስራኤል በሕዝብ በተጨናነቀችው ራፋ ላይ ሙሉ ወታደራዊ ዘመቻ እንዳታካሂድ እና እንዲሁም ከጦርነቱ በኋላ ሊከተል ስለሚችለው የሥርአት አልበኝነት አደጋ ዩናይትድ ስቴትስ

ያደረባትን ሥጋት አስመልክታ ብታስጠነቅቅም፣ የእስራኤል ኃይሎች በትላንትናው እለት ደቡባዊ ራፋን ጨምሮ ጋዛ ውስጥ ከሃማስ ጋር መዋጋት መቀጠላቸው ተዘግቧል።

"እስራኤል ራፋ ውስጥ በሰላማዊ ሰዎችን ከአደጋ መከላከል የሚያስችልም ሆነ፣ የጋዛው ጦርነት ሲያበቃ ሊፈጠር ስለሚችለው ሁኔታ አሳማኝ እቅድ መንደፏን ዋሽንግተን እስካሁን አላየችም" ያሉት የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊንከን ለኤንቢሲ የቴሌቭዥን ጣቢያ በሰጡት አስተያየት "እስራኤል ከጦርነቱ ማግስት የበርካታ የሃማስ ታጣቂዎች የሽምቅ ጥቃት፣ በሁከት የተሞላ እና ሥርዓተ አልበኝነት የነገሰበትን ሁኔታ የመውረስ እጣ ሊጠብቃት ይችላል" ብለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG