በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዕርዳታ ወደ ቬኔዝዌላ ተላከ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

በቀውስ ለተዋጠችው ቬኔዝዌላ የተላከ የውጭ ዕርዳታ የጫነ የዓለምቀፍ ቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ ፌዴሬሽን አውሮፕላን የመጀመሪያውን አቅርቦት ይዞ ዛሬ ካራካስ ገባ።

ዕርዳታው የገባው የፕሬዚዳንት ማዱሮ መንግሥት ከፌዴሬሽኑ ጋር ባለፈው ወር በደረሰበት ሥምምነት መሆኑ ታውቋል።

ከተጫነው ዕርዳታ መካከል ለሃገሪቱ እጅግ የሚያስፈልጓት መድኃኒቶችና ሌሎችም የሕክምናና ጤና አጠባበቅ አቅርቦቶች እንደሚገኙበት ተነግሯል።

ቬኔዝዌላ ውስጥ 650 የሚሆን ተረጂ የመድረስ ዕቅድ እንዳለው ዓለምቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG