በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኪሊማንጃሮ ተራራ የተነሳው እሳት


በኪሊማንጃሮ ተራራ የተነሳው እሳት
በኪሊማንጃሮ ተራራ የተነሳው እሳት

ከአፍሪካ በከፍታው ወደር በሌለው በኪሊማንጃሮ ተራራ ላይ የተነሳውን ቃጠሎ ለማጥፋት የታንዛኒያ የእሳት አደጋ ሰራተኞ እየተረባረቡ ነው።

የታንዛኒያ የቱሪዝም እና የተፈጥሮ ሃብቶች ሚኒስትሩ እንዳሉት እሳቱ አዕዋፍና ሌሎችም እንሥሳት የሚኖርበትን የተጠበቀ የተፈጥሮ አካባቢ ሊያወድመው ስጋት ፈጥሯል።

የእሳት አደጋ ሰራተኞች በተከታታይ ለአምስት ቀናት የያዙትን ጥረት ቃጠሎው ያለበት ስፍራ የአየሩ ሁኔታ ደረቅ መሆኑና ኃይለኛ ንፋስ አዳጋች አድርጎባቸዋል። በቃጠሎው በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት አልተዘገበም።

ቃጠሎው የተነሳው ለተራራ ወጪዎች ምግብ ለማብሰል እሳት ባቀጣጠሉ ሰራተኞች እንደሆነ ተዘግቦ የነበረ ሲሆን ይሁንና ምርመራው ቀጥሏል።

XS
SM
MD
LG