በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የክስ ሂደት ተደመደመ፣ ፕሬዚዳንት ትረምፕ ነፃ ተባሉ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

በተወካዮች ምክር ቤት ከቀረቡባቸው ክሶች ትናንት በመወሰኛው ምክር ቤት “ከክሱ ነፃ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ነፃ ወጡ” የሚል በትልልቁ የተፃፈበት ጋዜጣ በማውለብለብ የአሸናፊነት ደስታቸውን እየገለጹ፤ ተቺዎቻቸውን ደግሞ እየወረፉ ናቸው።

ዛሬ በአንድ ዋሽንግተን ውስጥ የሚገኝ ሆቴል በተካሄደ የብሄራዊ ፀሎት እና ቁርስ ሥነ ስርዓት ላይ የተገኙት ፕሬዚዳንቱ መወሰኛ ምክር ቤቱ ከሁለቱም ክሶች ነፃ እንዳደረጋቸው ዩኤስኤ ቱዴይ ጋዜጣ ላይ “አኩዊትድ ነፃ ተባሉ” የሚለውን ከፍ አድርገው አሳይተዋል።

የተወካዮች ምክር ቤት ዲሞክራቶች እርሳቸውን ከሥልጣን በሚያስወግድ ጥፋት ለመክሰስ ያደረጓቸው ጥረቶች ሲነቅፉ የከረሙት ትረምፕ ሃገራችን በእያንዳንድ ካህዲያን ብልሹ ሰዎች ምክንያት በብዙ መከራ ውስጥ አልፋለች ብለዋል።

ከክሶቹ ነፃ ያወጧቸውን “ጀግኖቹ ሪፖብሊካን ፖለቲከኞችና መሪዎች ሲሉ ያሞገሷቸው ትረምፕ፤ በሥልጣን አለአግባብ ተጠቅመዋል ብለው ድምፅ የሰጡትን ሪፖብሊካኑን ሴነተረ ሚት ሮምኒን በስም ሳይጠቅሱ አውግዘዋቸዋል።

ሮምኒ ትረምፕ ዩክሬይንን ዋና የምርጫ ተፎካካሪያቸው ምክትል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንን እንድትመረምር በመጠየቅ የፈፀሙትን ጥፋት ሃይማኖቱን በጥልቅ እንደሚያከብር ክሪስቲያን ሰው ችላ ልለው አይቻለኝም ብለዋል።

ትረምፕ ሃሰት እንደሆነ የሚያውቀውን ነገር በሃይማኖት የሚያሳብብ ሰው አልወድም ብለዋል።

የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤዋ ናንሲ ፐሎሲ የክሱ ሂደት እየቀጠለም ሳለ ለፕሬዚዳንቱ እፀልይላቸዋለሁ ይሉእንደነበር ሲታወስ ትረምፕ “ ዕውነት እንዳልሆነ እያወቀ እፀልይለታለሁ የሚል ሰውም አልወድም’ ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG