በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስምንት ፊሊፒናውያን በስቅለተ ክርስቶስ አምሳል በሚስማር ተቸንክረው ተሰቀሉ


የ62 ዓመቱ ሩበን ኢናጄ
የ62 ዓመቱ ሩበን ኢናጄ

የቱሪስት መስሕብ በኾነው ትዕይንት ለ34ኛ ጊዜ የተሰቀለ አለ

የኢየሱስ ክርስቶስን ስቅለት ተመስሎ ለማሳየት የቆረጡ ስምንት ፊሊፒናውያን፣ ከዕንጨት በተሠራ መስቀል ላይ በሚስማር ተቸንክረው የተሰቀሉ ሲኾን፣ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ድርጊቱን ኮንናለች።

በአምሳለ ስቅለተ ክርስቶስ፣ ለዐሥርት ዓመታት ሲደጋገም በቆየው በዚኹ ትዕይንት፣ 10 ሴንቲ ሜትር በሚኾን ሚስማር፣ የተሳታፊዎቹ እግራቸው እና እጃቸው በዕንጨት ላይ ከተቸነከረ በኋላ፣ ለ10 ደቂቃ ወይም ከዚያም በላይ እንደተሰቀሉ ይቆያሉ።

በሰሜናዊ ማኒላ በምትገኘው፣ ሳን ፔድሮ ኩቱድ በተሰኘችው መንደር በተከናወነው የአምሳለ ስቅለተ ክርስቶስ ሥነ ሥርዓት ላይ፣ የአካባቢውን ሰዎች ሳይጨምር፣ 15 ሺሕ ቱሪስቶች ተገኝተው ትዕይንቱን ተመልክተዋል።

ጦርነቱ፣ በኹለት አገሮች መካከል ቢካሔድም፣ የምግብ እና የነዳጅ ዋጋ በመናሩ፣ ዳፋው ለእኛ ተርፏል፤”

የ62 ዓመቱ ሩበን ኢናጄ፣ ከሚቸነከሩት አንዱ ነው። በዚኽ ዓመት፣ እጅ እና እግሩ በሚስማር ተወግቶ ሲቸነከር የአሁኑ ለ34ኛ ጊዜ ነው፡፡ በመስቀሉ ላይ ሳለም፣ ኮቪድ-19 እና በዩክሬን እየተካሔደ ያለው ጦርነት ማብቂያ እንዲኖረው መጸለዩን ተናግሯል። “ጦርነቱ፣ በኹለት አገሮች መካከል ቢካሔድም፣ የምግብ እና የነዳጅ ዋጋ በመናሩ፣ ዳፋው ለእኛ ተርፏል፤” ሲል ተደምጧል ኢናጄ። ኢናጄ፣ በአምሳለ ክርስቶስ የመሰቀል ልምምዱን የጀመረው፣ እ.አ.አ በ1985 ዓ.ም.፣ ከሦስተኛ ፎቅ ላይ ወድቆ በተኣምር ሕይወቱ በመትረፉ ምስጋና ለማቅረብ በሚል ነበር።

በፊሊፕንስ የሚገኙ የክርስትና ሃይማኖት መሪዎች፣ ለዓመታት ሲፈጸም የቆየውን ልምድ ያወግዛሉ። ይልቁንስ፣ ምእመናን ራሳቸውን ሳይጎዱ፣ እንደ ደም ልገሳ እና ሌሎች የሰብአዊ ረድኤት ሥራዎችን በማከናወን፣ እምነታቸውን ማሳየት ይችላሉ፤ በማለት ይመክራሉ።

XS
SM
MD
LG