በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም
አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም

ላለፉት 42 ዓመታት በመድረክ፣ በራድዮ፣ በቴሌቭዥን፣ በፊልም በርካታ የመድረክ የጥበብ ሥራዎች የሚታወቀው ተዋናይ ፍቃዱ ተክለማርያም ትላንት ምሽት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተገለፀ፡፡

ላለፉት 42 ዓመታት በመድረክ፣ በራድዮ፣ በቴሌቭዥን፣ በፊልም በርካታ የመድረክ የጥበብ ሥራዎች የሚታወቀው ተዋናይ ፍቃዱ ተክለማርያም ትላንት ምሽት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተገለፀ፡፡

ከወራት በፊት ሁለቱም ኩላሊቶቹ ከጥቅም ውጪ በመሆናቸው ንቅለ ተከላ እንደሚያስፈልገው መገለፁ ይታወሳል። የአርቲስቱ አስክሬን ከነበረበት የፀበል ቦታ ተነስቶ ወልዲያ ከደረሰ በኋላ አሸኛኘት ተደርጎለታል፡፡

በኦቴሎ፣ ኤዲፐስ ንጉሥ፣ ሐምሌት፣ ቴዎድሮስ፣ ንጉሥ ኦርማህ፣ የሰርጉ ዋዜማ፣ አቡጊዳ ቀይሶ፣ ባለካባ ባለዳባ፣ መልዕክተ ወዛደር የመድረክ ሥራዎቹ፤ በቴሌቪዥን ባለጉዳይ ፣ ገመና፣ መለከት እና በመሳሰሉት ሥራዎቹ ይታወቃል።

በኢትዮጵያ ራድዮ “ከመጽሃፍት ዓለም” በተሰኘው የራድዮ ፕሮግራም “ሞገደኛው ነውጤ፣ ጥቁር ደም፣ ሳቤላ፣ የነበረው እንዳልነበር” በተሰኙ አጫጭርና ረጅም ልቦለዶች ሥራዎቹ ይታወቃል፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG