በዩናይትድ ስቴይትስ ማእከላዊ የሚዙሪ ግዛት የ18 ዓመቱን አፍሪካ-አሜሪካዊ ወጣት በጥይት የገደለው ፖሊስ በወንጀል ተጠያቂ እንዳይሆን እንዳይጠየቅ ከወሰነ በኋላ በመላ ሃገሪቱ ተቃውሞዎች ተሰምተዋል።
ጉዳዩን የመረመረው ከሕዝቡ የተውጣጣ አካል (Grand Jury) ለሶስት ወራት ያህል፤ የፖሊስ ባልደረባው በግድያ ወንጀል ክስ ይመስረትበት ወይንም አይመስረትበት የሚለውን ሲሟገትበት ቆይቶ ነው፤ ትላንት ሰኞ ማታ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው።
በፍርድ ቤቱ ውሳኔ የተበሳጩ ሰልፈኞች ግን በፈርግሰን ተቃውሞ ሲያሰሙ፤ ሁከት ተቀስቅሷል፤ ንብረትም ወድሟል። ትናንት ምሽት ፈርግሰን ምዙሪ በእሳት ስትቃጠል ነው፤ ያመሸችው።
የከተማዋ ነዋሪዎች ተቃውሟቸውን የጀመሩት፤ የግራንድ ጁሪው የፖሊስ ባልደረባው ዳረን ዊልሰን ወጣቱን አፍሪካ አሜሪካዊ ማይክል ብራውንን ባለፈው ነሀሴ ወር ተኩሶ ከገደለ በኋላ፤ በወንጀል አይጠየቅም፤ ሲል ትናንት ማምሻውን ውሳኔውን ካሳለፈ በኋላ ነው።
በርዕሰ ጉዳዩ ዙሪያ የተጠናቀሩትን ዘገባዎች ከዚህ ያድምጡ፤