በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የብሄራዊ ደኅንነት ምክር ቤት መግለጫ


በኢትዮጵያ ዙርያ የተከሰተውን የሰላም መደፍረስ ለማረጋጋትና ዜጎች የሰላም ዋስትና እንዲያገኙ የፌደራልና የክልል የፀጥታ አስከባሪ ተቋማት አስፈላጊውን ህጋዊና ተመጣጣኝ እርምጃ እንዲወስዱ ትዕዛዝ መተላለፉን የብሄራዊ ደኅንነት ምክር ቤት አስታወቀ።

ብሄራዊ የደኅንነት ምክር ቤቱ በመላ ሀገሪቱ እየተስተዋሉ ያሉ የሰላም መደፍረሶችን በአጠቃላይም በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደርና ሰሜን ሸዋ ዞን አዋሳኝ አካባቢዎች ያለውን የሰላም መደፍረስ በተለየ ትኩረት በመገምገም መግለጫ አውጥቷል፡፡

በመግለጫውም በከሚሴና አጎራባች አካባቢዎች የተከሰተውን የሰው ህይወት መጥፋትና ንብረት ተቀባይነት የሌለው ተግባር መሆኑን አስገንዝቧል። በግጭቱ ህይወታቸውን ላጡ፣ አካላቸው ለጎደለና ንብረታቸው ለወደመባቸው ሁሉ ምክር ቤቱ የተሰማውን ሀዘን ገልጿል። ዜጎች በሰላም የመኖር ዋስትና እንዲኖራቸው ማድረግና የህግ የበላይነት ማስፈን የመንግሥት ዋነኛ ኃላፊነት መሆኑን ጠቅሷል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ብጥብጡን ያቀናበሩት፣ ያነሳሱትና የፈጸሙትን አካላት ለህግ የማቅረቡ ሥራም በከፍተኛ ትኩረት ይሰራበታል ይላል መግለጫው። ለዚህም ጥናት የሚያደርግ ቡድን ከፌደራል ተቋማትና ከክልሉ መሰማራቱን ገልጿል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG