በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፖሊስ የነገው ሰልፍ ሕገ-ወጥ ነው አለ፤ አቶ ጀዋር ጤና መሆናቸውን ገለፀ


አዲስ አበባ
አዲስ አበባ

"12፣12፣12" በሚል ስም ለገ ነሐሴ 12 ቀን 2012 ዓ.ም የተጠራው ሰልፍ ሕገ-ወጥ እና የጥሪው ዓላማም ፀረ-ሰላም በመሆኑ ኅብረተሰቡ ለዚህ ስልፍ ተባባሪ እንዳይሆን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አሳሰበ።

በሌላ በኩል "አቶ ጀዋር መሐመድ ታሟል፤ ችግር ደርሶበታል" ተብሎ በተለያዩ የሚዲያ አውታሮች የሚወራው ሐሰተኛ መረጃ መሆኑን እና ግለሰቡ በተሟላ ጤንነት ላይ የሚገኝ መሆኑን የፖሊስ ኮሚሽኑ ገልጿል።

በመሆኑም በዚህ ሰበብ ሰውን እያወናበዱ በሐሰተኛ ወሬ የፍርድ ሂደቱን ለማዛባት የሚደረገው ጥረት በማንኛውም ሁኔታ ተቀባይነት የሌለው ተግባር መሆኑን ኅበረተሰቡ ተገንዝቦ ለሕገወጥ ጥሪዎች እና ቅስቀሳዎች ተባባሪ እንዳይሆን አሳስቧል።

ኅብረተሰቡ ሰላምና ፀጥታ በማስከበር ተግባር ላይ ከተሰማሩ የፀጥታ ኃይሎች ጎን ተሰልፎ ሰላሙን እንዲጠብቅ ኮሚሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል።

በሌላ ዜና የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ባወጣው በወቅታዊ ሃገራዊና የፓርቲ ጉዳዮች ላይ በመወያየት አቅጣጫ ማስቀመጡ ተዘግቧል። ከውይይቱ ባወጣው መግለጫ ፈተናን ወደ ጥንካሬ እየቀየርን የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን እናደርጋለን ብሏል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ፖሊስ የነገው ሰልፍ ሕገ-ወጥ ነው አለ፤ አቶ ጀዋር ጤና መሆናቸውን ገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:29 0:00


XS
SM
MD
LG