በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዲሱ የፍልሰት ህግ በተግባር እንዳይውል የሚከለክል ጊዚያዊ ትዕዛዝ ተላለፈ

ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ፌደራል ዳኛ የትረምፕ አስተዳደር ያወጣው ጥገኝነት ጠያቂዎችን የሚያግድ አዲስ የፍልሰት ህግ በተግባር ላይ እንዳይውል የሚከለክል ጊዜያዊ ትዕዛዝ አስተላለፈዋል። እንዳይተገበር የታገደው አዲስ የኢሚግረሽን ህግ በተመደበው ድንበር በኩል ያልገቡት መጤዎች ጥገኝነት እንዳይጠቁ የሚከለክል ነው።

አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ፌደራል ዳኛ የትረምፕ አስተዳደር ያወጣው ጥገኝነት ጠያቂዎችን የሚያግድ አዲስ የፍልሰት ህግ በተግባር ላይ እንዳይውል የሚከለክል ጊዜያዊ ትዕዛዝ አስተላለፈዋል። እንዳይተገበር የታገደው አዲስ የኢሚግረሽን ህግ በተመደበው ድንበር በኩል ያልገቡት መጤዎች ጥገኝነት እንዳይጠቁ የሚከለክል ነው።

ፕረዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ህጉን ያወጡት ከ12 ቀናት በፊት ሲሆን በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ዩናይትድ ስቴትስንና ሜክሲኮን በሚያዋስነው ድንበር ይገባሉ ተብለው የሚጠበቁትን ፍልሰተኞች ለማገድ የታቀደ ነው።

የአሜሪካ የሲቪል አርነት ማኅበርና ሌሎች ቡድኖች ታድያ ጉዳዩ በፍርድ ቤት እስከሚታይበት ጊዜ ድረስ አዲሱ ህግ እንዳይተገበር በፍጥነት የህግ ተግዳሮት አስገቡ።

ጆን ቲጋር የተባሉ ፌደራል ዳኛ በማንኛውም የዩናይትድ ስቴትስ ድንበር የገባ ሰው ጥገኝነት መጠየቅ እንደሚችል የኢሚግረሽንና የዜግነት ህግ የሚፈቅድ መሆኑን በመግለጽ አዲሱ የትረምፕ አስተዳደር ህግ ይህን ይፅረራል በማለት ፍርድ ቤት እስከሚቀርብበት ጊዜ ድረስ አግደውታል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG