በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያ ቱጃሮች ምዕራባውያኑ ከሚወስዱትን እርምጃ ለማምለጥ ሃብታቸውን ለማሸሽ ዓይናቸውን ዱባይ ላይ መጣላችው ተነገረ


ፎቶ ፋይል - ዱባይ እአአ ታህሣሥ 21/2009
ፎቶ ፋይል - ዱባይ እአአ ታህሣሥ 21/2009

የሩስያን የዩክሬንን ወረራ ተከትሎ ምዕራባውያን ሃገሮች በሞስኮ ላይ ከጣሏቸው እና እየበረቱ ከመጡት ማዕቀቦች ለመከለል ባለ ጸጋ ሩሲያውያን ሃብታቸውን ከአውሮፓ ወደ ዱባይ ለማዘዋወር እየጣሩ መሆናቸውን የሕግ እና የፋይናንስ መረጃ ምንጮች ጠቆሙ።

እምብዛም ሕጎች እና ደምቦች የማይከበሩባት የባህረ ሰላጤው የፋይናንስ እና የንግድ ማዕከል የሆነችው ዱባይ ለዓለማችን ቱባ ባለቱጃሮች ልዩ መስሕብ ሆና መቆየቷም ይታወቃል። አሁንም ከምዕራባውያኑ አጋሮቿ እና ከሞስኮ ከአንዳቸውም ጎን ያለመሰለፍ ፍላጎት ያንጸባረቀቸው የተባበሩት አረብ ኤሚሬት ዝንባሌ ሩሲያውያኑ ለገንዘባቸው የተሻለ ዋስትና ከዚያ እንደሚያገኙ እምነት እንዲያድርባቸው ማድረጉ ነው የተዘገበው።

ባለፉት ዓመታት ውስጥ ከሩሲያ ጋር ያላትን ግንኙነት ይበልጥ እያጠናከረች የመጣችው የተባበሩት አረብ ኢሚሬት ምዕራባውያኑ በሞስኮ ላይ የጣሏቸውን ማዕቀቦች የሚስተካከል እርምጃ ካልመውሰዷም ባሻገር ማዕከላዊ ባንኳም ማዕቀቦቹን በተመለከተ ለሃገሪቱ ባንኮች እና ተቋት እስካሁን መመሪያ ያለመስጠ ተጠቁሟል።

ሩሲያውያኑ ባለ ጸጎች ገንዘባቸውን በአሁኑ ወቅት በሩስያ ተቋማት፣ የንግድ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ላይ የተጣሉትን ማዕቀቦች ተግባራዊ በሚያደርጉት በስዊዘርላንድ ወይም በለንደን የሚገኙ ባንኮች ገንዘብ ወደ ዱባይ ለማዛወር እየጣሩም መሆናቸውን የአንድ ግዙፍ የስዊስ የግል ባንክ አንድ ከፍተኛ የባንክ ባለ ሞያ እና ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ የሕግ ሰው ተናገሩ።

ዋና መቀመጫጨውን በዱባይ የያደረጉት የሕግ ሰው፣ ድርጅታቸው በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር የሚያወጣ “ሃብት”በምን ያህል ፍጥነት ወደ ባህረ ሰላጤዋ አረብ ሃገር ማዛወር ይቻላል” የሚሉ ጥያቄዎች የሩሲያ መሰረት ካላቸው ድርጅቶች እየደረሳቸው መሆኑን ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG