በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፋይዘር 3ኛው የማጠናከሪያ ክትባት ፈቃድ እየታየ ነው


የኮቪድ 19 ክትባት
የኮቪድ 19 ክትባት

ትናንት ረቡዕ የዩናይትድ ስቴትስ የምግብና የመድሃኒት አስተዳደር ወይም ኤፍዲኤ ባደረገው ግምገማ፣ ለሦስተኛ ጊዜ የሚወሰደው የፋይዘር የኮቪድ 19 ማጠናከሪያ ክትባት፣ የሰዎችን የመከላከል አቅም፣ ከፍ የሚያደርግ ነው ሲል፣ አሁን በመወሰድ ላይ የሚገኘውም ከፍተኛ ህመም እንዳይፈጠር በማድረግ ረገድ፣ በቂ አገልግሎት እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡

የምግብና የመድሃኒት አስተዳደሩ፣ ፋይዘር፣ ቀደም ሲል የተሰጡት ክትባቶች ውጤታማነት ከስድስት እስከ ስምንት ወራት ከተወሰዱ በኋላ የመከላከል አቅማቸው እየተመናመነ ስለሚመጣ ሶስተኛውን የማጠናከሪያ ክትባት ለመሰጠት እንዲችል ያቀረበውን ጥያቄ እየተመለከተው መሆኑን አስታውቋል፡፡

ፋይዘር በ300 ሰዎች ላይ ያደረገው ሙከራ የመከላከል አቅማቸውን ካለፉት ክትባቶች ይልቅ ከሶስት እስከ አምስት እጅ በላይ ከፍ እንደሚያደርገው ገልጿል፡፡

ይሁን እንጂ የምግብና የመድሃኒት አስተዳደሩ ባወጣው መግለጫ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ህጋዊ ፈቃድ ተሰጥቷቸው እየተሰጡ ያሉ ክትባቶች የከፋውን የኮቪድ 19ን ቫይረሰም ሆነ ተከትሎ የሚመጣውን ሞትን አሁን ድረስ መከላከል ይችላሉ ብሏል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የመድሃኒት ቁጥጥር አማካሪ ኮሚቴ ፋይዘር ሶስተኛው ዙር የማጠናከሪያ ክትባት ለመስጠት የጠየቀውን ፈቃድ እንዲሰጠው ለመሰወን በነገው እለት ይሰበሰባል፡፡

XS
SM
MD
LG