በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፋይዘር ኩባኒያ ለተሰራው የኮቪድ-19 ክትባት ሥራ ላይ እንዲውል ፈቃድ ተሰጠ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት የምግብ እና የመድሃኒት አስተዳደር (ኤፍዲኤ) በፋይዘር ኩባኒያ ለተሰራው የኮቪድ አስራ ዘጠኝ ክትባት ሥራ ላይ እንዲውል ሙሉ ፈቃድ ሰጠ።

ፋይዘር እና ባዮንቴክ ሉባኒያዎች የሰሩት ክትባት እስካሁን ጥቅም ላይ የዋለው ኤፍዲኤ በአጣዳፊ ሁኔታ ስራ ላይ እንዲውል በሰጠው ፈቃድ ነበር።

የዩናይትድ ስቴትስ የምግብ እና የመድሃኒት አስተዳደር ተጠባባቂ አስተዳዳሪ ጃኔት ዉድኮክ ሙሉ ፈቃድ መሰጠቱን አስመልክተው ዛሬ ባወጡት መግለጫ

" ይህ ክትባት በኤፍ ዲ ኤ የሚፈለግበትን ደህንነትን፥ ውጤታማነትንን እና የምርት ጥራትን የሚመለከቱትን ከፍተኛ መስፈርቶች በሚገባ ያሟላ መሆኑን ህዝቡ በሚገባ ሊተማመንበት ይችላል" ብለዋል።

እስካሁን ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ሁለት መቶ ሚሊዮን በዐለም ዙሪያም በብዙ መቶ ሚሊዮኖች የተቆጠሩ የፋይዘር ክትባቶች ስራ ላይ ውለዋል።

በኮቪድ 19 ዓለም አቀፍ ዜና

ታይዋን የአገር ውስጥ የኮቪድ ክትባት ዘመቻ የጀመረች ሲሆን፣ የኒውዘላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ደግሞ ቦኮቪድ 19ኙ የዴልታ ቫይረስ ዝርያ ስርጭት የተነሳ በአገሪቱ በጠቅላላ የተጣለው የማህበራዊ እንስቃሴዎች ገደብ ቢያንስ እስከ አርብ ድረስ የተራዘመ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የቻይና ጤና መምሪያ ዛሬ ሰኞ ባወጣው መግለጫ፣ ከሀምሌ ወር ጀምሮ በአገሪቱ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስ የተመዘገበ የኮቪድ 19 ተጋላጭ አለመኖሩን አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG