በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካ ፌደራል የምርመራ ቢሮ የሂለሪ ክሊንተን ኢመይል ልውውጥ በሚመለክት ሰፊ ምርመራ ማድረጉን ገልጿል


ሂላሪ ክሊንተን(ግራ) እና የፌደራሉ ምርመራ ቢሮ ስራ አስኪያጅ ጄምስ ኮመይ(ቀኝ)
ሂላሪ ክሊንተን(ግራ) እና የፌደራሉ ምርመራ ቢሮ ስራ አስኪያጅ ጄምስ ኮመይ(ቀኝ)

የዩናይትድ ስቴትስ ፌደራል የምርመራ ቢሮ ሂለሪ ክሊንተን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት የኢመይል ልውውጣቸውን በመንግስታዊ ሳይሆን በግል ተንቀሳቃሽ ስልክ መጠቀማቸውን በሚመለክት ሰፊ ምርመራ ማድረጉን ገልጿል።

ጽ/ቤቱ የግል ስልክ መጠቀም ሚስጢራዊ ሰነዶችን ለስርቆት የሚያመች በመሆኑ እጅግ ግድየለሽ የሆነ አያያዝ ነው ሲል ክፉኛ ነቅፏቸዋል ይሁንና የወንጀል ክስ ሊመሰርትባቸው የሚያስችል ድረስ የሄደ አይደለም ሲሉ የፌደራሉ ምርመራ ቢሮ ስራ አስኪያጅ ጄምስ ኮመይ አስታውቀዋል።

የምርመራው ቢሮ ስራ አስኪያጅ ጄምስ ኮመይ ሂለሪ ክሊንተን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት የግል ኢመይል በመጠቀማቸው ዙርያ ሰፊ ምርመራ ከተደረገ በኋላ በሳቸው ላይ ክስ እንዲመሰረት ምክረ-ሀሳብ እንደማያቀርቡ አስታውቀዋል።

“አቃቤ-ህግ በሂለሪ ክሊንተን ላይ ክስ ለመመስረትም ሆነ ላለመመስረት ከመወሰናቸው በፊት የተለየዩ ነገሮችን አስላስለዋል። በተለይም ቸልተኝነቱ ሆን ብሎ የተደረገ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ነጥብ በሚገባ አጢነዋል። የአንድ ሰው ተግባርንና ከዚህ ቀደም የታዩ ተመሳሳይ ድርጊቶች አያያዝንም ተመልክተዋል። የአያያዝ ጉድለቱንና የሚስጢራዊ መረጃዎች መደምሰስን ስንመረምር በነሱ ላይ ተንተርሶ ክስ ለመመስረት የሚያስችል ጉዳይ አላገኘንም።”

የፌደራሉ ምርመራ ቢሮ ስራ አስኪያጅ ጄምስ ኮመይ
የፌደራሉ ምርመራ ቢሮ ስራ አስኪያጅ ጄምስ ኮመይ

ጄምስ ኮመይ አያይዘው ግን የተደረገው ምርመራ ሂለሪ ክሊንተና በሳቸው ስር የሚሰሩት ሰዎች በሚስጢራዊ መረጃ አያያዝ ላይ ቸልተኝነትን አሳይተዋል። ህግ የመጣስ መሰረት ማስረጃም አለ ብለዋል።

110 ኢመይሎችና 52 የኢመይል ሰንሰለቶች በተላኩበት ወቅት ሚስጢራዊ መረጃ እንደነበራቸው ታውቋል። ከነሱም አንዳንዶቹ ከፍተኛ ሚስጢር ነበሩ። ይሁንና ድርጊቱ ሆን ብሎ የተፈጸመ አይደለም ብለዋል የምርመራው ቢሮ ዳይረክተር።

በሂለሪ ክሊንተን ላይ የወንጀል ክስ ባለመመስረቱ የተበሳጩት ሪፑብሊካዊው ተቀናቃኛቸው ዶናልድ ትራሞፕ ሰሜን ካሮላይና ሆነው ሲናገሩ የፌደራሉ የምርመራ ቢሮ ውሳኔ “ያስፍራል” ብለዋል።

“የናንተን አላውቅም። እኔ ግን ምን ጊዜም ቢሆን ሂለሪ ክሊንተን በአደገኛውና በህገ-ወጡ ተግባራቸው ከወንጀል ክስ እንደሚያመልጡ ይሰማኝ ነበር። ስርአታችን ብልሹ መሆኑ ያሳዝናል።”

ሂለሪ ክሊንተን ከኦፌሴላዊው ኢመይል ይልቅ ከግል የኮምፑተር አገልግሎት ጋር የተያያዘውን ኢመይል የተጠቀሙት የግል የመረጃ ልውውጦቹን ደህንነት ለመጠበቅ ስለፈለጉ እንደሆነ ተናግረዋል።

የፌደራሉ የምርመራ ቢሮ ዳይረክተር ኮመይ ግን ጠላት ወገኖች ለክሊንተን ኢመይል ተደራሽነት ሊያገኙ የሚችሉበት እድል ነበረ ይላሉ።

በእንደዚህ አይነቱ አሰራር መገልገሉ በመንግስት ኢመይል ከመጠቀም የባሰ የተጋለጠ መሆኑን ተንታኞች ይናገራሉ።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የአሜሪካ ፌደራል የምርመራ ቢሮ የሂለሪ ክሊንተን ኢመይል ልውውጥ በሚመለክት ሰፊ ምርመራ ማድረጉን ገልጿል
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:23 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG