በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፋዉቺ ጡረታ ሊወጡ ነው


ፎቶ ፋይል፦ በተላላፊ በሽታዎች ላይ የሚካሄደው ምርምርና ቁጥጥር ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑትና ዩናይትድ ስቴትስ ያካሄደችው ፀረ ኮቪድ 19 ዘመቻ መሪ ተዋናይ የነበሩት ዶ/ር አንተኒ ፋዉቺ
ፎቶ ፋይል፦ በተላላፊ በሽታዎች ላይ የሚካሄደው ምርምርና ቁጥጥር ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑትና ዩናይትድ ስቴትስ ያካሄደችው ፀረ ኮቪድ 19 ዘመቻ መሪ ተዋናይ የነበሩት ዶ/ር አንተኒ ፋዉቺ

በተላላፊ በሽታዎች ላይ የሚካሄደው ምርምርና ቁጥጥር ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑትና ዩናይትድ ስቴትስ ያካሄደችው ፀረ ኮቪድ 19 ዘመቻ መሪ ተዋናይ የነበሩት ዶ/ር አንተኒ ፋዉቺ በዚህ ዓመት መጨረሻ በጡረታ እንደሚገለሉ አስታውቀዋል።

የ81 ዓመቱ ፋዉቺ የሃገሪቱን ብሄራዊ የሰውነት መቆጣት (አለርጂ)ና የተላላፊ በሽታዎች ተቋም ላለፉ 38 ዓመታት የመሩ ሲሆን ከሁለት ዓመት በላይ ለሚሆን ጊዜ የሁለቱ ተከታታይ ፕሬዚዳንቶች የኮቪድ-19 አማካሪም ሆነው እያገለገሉ ነው።

ፋዉቺ አሜሪካዊያን እንዲከተቡ አበክረው የመከሩና የታገሉ ሲሆን አብዛኞች ምክራቸውን መቀበላቸው ይነገራል።

በሌላ በኩል ግን ፋዉቺ በኮቪድ-19 ይደርስ የነበረውን የሞት መጠን ‘ዝቅ አድርገው ገምተዋል’፤ በኋላም የኮሮናቫይረስ ተፈጥሮና ጠባይ ይበልጥ ሲታወቅ በወረርሽኙ መጀመሪያ አካባቢ ‘ከቤት ውጭ ማስክ ማድረግ አያስፈልግም’ ብለዋል በሚል ለትችት ተዳርገው ነበር።

ፋዉቺ ሰባት የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶችን አማክረዋል።

የፋዉቺን ጡረታ መውጣት የሰሙት ባይደን “ዶ/ር ፋውቺ ባበረከቱት የኅብረተሰብ ጤና አገልግሎት፣ በአሜሪካም ሆነ በዓለም ህይወትን ማዳን ተችሏል” ብለዋል።

XS
SM
MD
LG