በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የራያና ቆቦ ገበሬዎች ስጋታቸውን ገልጸዋል


ራያ ቆቦ
ራያ ቆቦ

በራያና ቆቦ የሚኖሩ ገበሬዎች ከመንግስት በቂ የእህል እርዳታ ካላገኘን፥ ለከባድ የረሃብ አዳጋ እንጋለጣለን ብለው ይፈራሉ።

በራያና ቆቦ፥ ልዩ ስሙ "መንደፈራ" በተባለው አከባቢ የሚኖሩ ገበሬዎች፥ በድርቁ ምክንያት ከደረሰባቸው ረሃብ ለማምለጥ፥ ምግብ የሚገዙት ከብቶቻቸውን እየሸጡ እንደሆነ ይናገራሉ።

በአከባቢው በአሁኑ ሰዓት እየጣለ ያለው ዝናብ፥ ዘሩን ይመልስልናል ያሉትን እህል እንዳያበላሽባቸውም ኩፉኛ ሰግተዋል።

ከመንግስት በቂ የእህል እርዳታ ካላገኘን፥ ለከባድ የረሃብ አዳጋ እንጋለጣለን ብለው ይፈራሉ።

በሰሜን ወሎ ዞን የኣደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበርያ ፅህፈት ቤት ተጠሪ አቶ መሐመድ ያሲን ደግሞ በዞኑ ለ54 ሺህ ህዝብ የእህል እርዳታ እንደተሰጠና፥ መንግስት በቂ የእህል ክምችት እንዳለው ይናገራሉ።

ግርማይ ገብሩ ከቆቦ የላከውን ዘገባ ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

የራያና ቆቦ ገበሬዎች ስጋታቸውን ገልጸዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:34 0:00

XS
SM
MD
LG