ግድያ ሲፈጸም ያሳያሉ የተባሉ እና በቅርቡ በሶሻል ሚዲያ የተለቀቁ ቪኦኤ ያላረጋገጣቸው የቪዲዮ ክሊፖችን በተመለከተ የፋኖ ታጣቂ ቡድን እጁ እንደሌለበት አስታውቋል።
የፌዴራል እና የክልል ባለሥልጣናት ግን “የጭካኔ ድርጊት” ብለው የገለጹትንና በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ ተገድሏል የተባለውን ወጣት በተመለከተ ባለፈው ሐሙስ ዕለት በጽኑ አውግዘዋል።
በአማራ ክልል የትጥቅ ትግል በማካሄድ ላይ ከሚገኙት ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው ‘የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት’ መሪ እንደሆኑ የነገሩን አቶ እስክንድር ነጋ፣ በቪዲዮ ላይ ግድያ ያሳያል የተባለውን ድርጊት በተመለከተ ቡድኑ ተጠያቂ እንዳልሆነ አስታውቀዋል።
መድረክ / ፎረም