በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በእስራኤል - ሐማስ ግጭት ውስጥ የጠፉ አሜሪካውያን ቤተሰብ አባላት መግለጫ ሰጡ


በእስራኤል - ሐማስ ግጭት ውስጥ የጠፉ አሜሪካውያን ቤተሰብ አባላት መግለጫ ሰጡ
በእስራኤል - ሐማስ ግጭት ውስጥ የጠፉ አሜሪካውያን ቤተሰብ አባላት መግለጫ ሰጡ

በእስራኤል ውስጥ የጠፉ የበርካታ አሜሪካውያን ቤተሰብ አባላት፣ ዘመዶቻቸውን ለማግኘት የሚደረገው ፍለጋ እንዲጠናከር፣ ለባለሥልጣናት ጥሪ አቅርበዋል።

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ፣ ሐማስ በእስራኤል ላይ ባደረሰው ጥቃት፣ ቢያንስ ዘጠኝ የአሜሪካ ዜጎች እንደተገደሉ፣ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። መሥሪያ ቤቱ አክሎም፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የአሜሪካ ዜጎች እንደጠፉና የት እንዳሉ እንደማይታወቅም አመልክቷል።

በእስራኤል ቴል አቪቭ ከተማ በተካሔደ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተገኘውና ያሉበት ያልታወቀ አንድ አሜሪካዊ ልጅ ናሃር ኔታ፣ የእስራኤል መንግሥት፣ በሐማስ የታገቱትን ሰዎች የማስመለስ ግዴታ እንዳለበት ተናግሯል።

“የዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር፣ ፕሬዚዳንት ባይደንና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከንም፣ እዚኽ ላለው እያንዳንዱ የአሜሪካ ዜጋ ሕይወት ሓላፊነት አለባቸው፤” ያሉት ኔታ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎችን በሰላም ወደ ቤታቸው ለመመለስ ያለባቸውን ሓላፊነት እንዲወጡ ጠይቋል።

በተመሳሳይ ሪቻል ጎልድበርግ የተባሉ ልጃቸው የጠፋባቸው ሌላ እናትም፣ ልጃቸው፣ ቅዳሜ ዕለት በሐማስ ታጣቂዎች ጥቃት በተፈጸመበት የሙዚቃ ድግስ ላይ ታዳሚ እንደነበር ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

የጠፉት አሜሪካውያን፥ ታግተው፣ ተገድለው ወይም ተደብቀው እንደኾነ፣ እስከ አሁን በግልጽ የታወቀ ነገር የለም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG