በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ለህጻናት ተጠቃሚዎች አዲስ እቅድ አውጥቻለሁ” ፌስቡክ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ፌስቡክ በሚሰጠው አገልግሎት “ህጻናትን የሚጎዱ የተለያዩ መድረኮችን ያመቻቻል” በሚል ሰሞኑንን የቀረበበትን ውግዘትና ተጠያቂነት ተከትሎ የተለያዩ የማሻሻያ እርጃዎችን እንደሚወስድ አስታውቋል፡፡

መሠረቱን በካሊፎኒያ ሚንሎ ፓርክ ያደረገው የፌስቡክ ኩባንያ፣ እንደ ኢንስታግራም ባሉት የምስልና ፎቶዎች መቀባበያ መድረኮቹ፣ ህጻናት በተከታታይ ከሚመለከቷቸው ምስሎች ፋታ እንዲወስዱና እንዲገቱ የሚያደርጉ የተለያዩ ቅንብሮችን መጠቀም እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡

በተለይም ህጻናት መመልከት የማይገባቸውን ምስል ደጋግመው እንዳይመለከቱ የሚያግዳቸው መሆኑንም ገልጿል፡፡

ታዳጊዎቹ ወጣቶች ኢንተርኔት ላይ ምን እንደሚያደርጉ ምን እንደሚመለከቱ ማወቅ ለሚፈልጉ ወላጆችና ሞግዚቶቻቸውም በቤተሰቦቻቸው ምርጫ የተለያዩ የመቆጣጠሪያ ስልቶችን እንደሚያበጅ ፌስቡክ አስታውቋል፡፡

ይሁን እንጂ ይህ እቅዱ የመጣው “ኢንስትግራም ፎር ኪድስ” በሚል ልጆች ላይ ያነጣጠረ ልዩ ፕሮጀክቱን ባላፈው ወር መገባደጃ ላይ ለጊዜው ያቆመው መሆኑን ካስታወቀ በኋላ ነው፡፡

በዚህ የተነሳ ተችዎች ፌስቡክ አደረገዋለሁ ያላቸውን ስለማድረጉ ጥርጥሬ ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ምክንያቱም ተችዎቹ እንደሚሉት ስለ እቅዱ “በዝርዝር ያስቀመጠው ምንም ነገር የለም፡፡”

ፌስቡክ ግን ባለፉት ጥቂት ዓመታት ለአገልግሎት መድረኩ ደህንነት መጠበቂያ 13 ቢሊዮን ዶላር ያወጣ ሲሆን ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግም 40ሺ ሠራተኞች የተሰማሩበት መሆኑን አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG