በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፌስቡክ አቤቱታ ላቀረቡበት ከሳሾች የገንዘብ መቀጮ እና የደመወዝ ክፍያ ተወሰነበት


ፌስቡክ ኩባኒያ “ከውጭ ሀገር ለሚያስመጣቸው ሠራተኞች በማድላት፣ በደል ፈጽሞብናል” የሚል አቤቱታ ላቀረቡበት ከሳሾች 9 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ውዝፍ ክፍያ እና 4ሚሊዮን ሰባት መቶ ሽህ ዶላር መቀጮ እንዲከፍል የተወሰነበት መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ የፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ፌስቡክ መቀጮው እና የደመወዝ ክፍያው የተወሰነበት ቢያንስ እአአ ከ2018 መጀመሪያ አንስቶ እስከ ቀጠለው 2019 መስከረም ወር በነበረው ጊዜ ውስጥ በፈጸመው አድልዎ ምክንያት ነው ሲል የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አመልክቷል።

ኩባኒያው በጊዜያዊ የሥራ ፈቃድ ሰራተኞችን ለማምጣት ብሎ የአሜርካ ዜጎች፣ ስደተኞች እና ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸውን ሰዎች ጨምሮ በሀገር ውስጥ ለመቀጠር የሚያመለክቱ ሰዎችን በብዛት ሳይቀበል ቀርቷል ተብሎ ተወንጅሏል።

ፌስቡክ በጊዜያዊ የሥራ ፈቃድ የሚያስመጣቸውን ሰራተኞች ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ /ግሪን ካርድ/ እንዲያገኙ ሲረዳ መቆየቱን ዜናው ጠቅሷል።

ኩባንያው ለሠራተኞቹ አድልዎን በተመለከቱ ደንቦች፣ ሥልጠና ሊሰጥ እና ለክፍት የሥራ ቦታዎች የሚያመለክቱ ባለሙያዎች ምልመላ ሥርዓቱን ሰፋ ለማድረግ መስማማቱ ተገልጿል።

በፊስቡክ ኩባኒያ ላይ የተጣለው መቀጮ እና የደመወዝ ክፍያ በፍትህ ሚኒስቴር የሲቪል መብቶች ክፍል የሰላሳ አምስት ዓመት ታሪክ፣ ከፍተኛው መሆኑ ተዘግቧል።

የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ክሪስቲን ክላርክ በሰጡት ቃል "ፌስቡክ ከህግ በላይ አይደለም፤ የሀገራችንን የሲቪል መብቶች ህግ ማክበር አለበት" ብለዋል።

XS
SM
MD
LG