አዲስ አበባ —
መንግሥትና ፖለቲካ ፓርቲን ያልለየ የምርጫ ቅስቀሳ እየተካሄደ መሆኑን የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ኢዜማ አስታወቀ፡፡
የህዝብ ሃብትና ንብረት ለፓርቲ የፖለቲካ ቅስቀሳ ሥራ እየዋለ ነው ሲል ይከሳል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያ ውስጥ ስር የሰደደው የብሔር ፖለቲካ ህብረ ብሔራዊ አቋም ባላቸው የፖለቲካ ቡድኖች የምርጫ ቅስቀሳ ላይ ተጽእኖ እያሳረፈ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡
ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በበኩሉ ከምርጫ እንቅስቃሴ ጋር ተያይዘው የሚነሱ የአፈጻጸም ችግሮችን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።