በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአፍጋኒስታን ካቡል የቦንብ ፍንዳታ ደረሰ


በቦምብ ፍንዳታው ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል
በቦምብ ፍንዳታው ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል

በአፍጋኒስታንካቡል አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ ዛሬ የቦምብ ፍንዳታ መድረሱና ቁጥራቸው ባልታወቁ ሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሱን የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር፣ ፔንታገን፣ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

የፔንታገንቃል አቀባይ ጆን ከርቢ በሰጡት መግለጫ፣ ፍንዳታው የደረሰው፣ አቢ በር እየተባለ ከሚጠራው የካቡል አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ ነው፡፡

ቦታው አፍጋኒስታን ታሊባንን ከተቆጣጠረ በኋላ አገሪቱን ለቀውለመውጣት የሚሞክሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሰሞኑን የሚሰብሰቡበት መሆኑን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡

የታሊባንከፍተኛ ባለሥልጣን ለቪኦኤ እንደተናገሩት፣ ፍንዳታው የደረሰውአንድ አጥፍቶ ጠፊ፣ ከአውሮፕላን ማረፊያውውጭ፣ ሴቶችን ጨምሮበርካታ ሰዎች በተሰባሰቡበት ቦታ፣ ራሱንበማፈንዳቱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የመረጃምንጮች ለቪኦኤ እንደተናገሩት፣ ሌላ ሁለተኛፍንዳታም ከአውሮፕላን ማረፊያው 200ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው ባረን ሆቴል አቅራቢያ፣ መፈንዳቱን ገልጸዋል፡፡

ስለፍንዳታው ተጨማሪ ማብራሪያ ያልተሰጠ ሲሆን፣ እስካሁን ኃላፊነቱንየወሰደ ወገንም የለም፡፡

እንግሊዝና አውስትራሊያን ጨምሮ ምዕራባዊያን መንግሥታት፣ዛሬ ሀሙስ፣ በአውሮፕላንማረፊያው አቅራቢያ የሽብር ጥቃት ሊኖር እንደሚችል በመግለጽ፣ ከአገር ለቀውለመውጣት በቦታው የተሰባሰቡ ሰዎች፣ ሌላሰላማዊ ወደ ሆነ ቦታ እንዲወሰዱ ሲያስጠነቅቁ መቆየታቸውም ተመልክቷል፡፡

በፍንዳታውጉዳት የደረሰብቸው በርካታ ሰዎች፣ ቀደም ሲልፈንጅዎችና የጦር ጉዳት የደረሰባቸውቁስለኞች ወደ ሚታከሙበትና፣ መንግሥታዊ ባልሆነ የዓለም አቀፍ ተቋማት ባለቤትነት ይተዳደር ወደ ነበረው ሆስፒታል፣ መወሰዳቸው ተመልክቷል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በጉዳዩ ላይ ከጸጥታ ባለስልጣኖቻቸው ጋር ስብሰባ አድርገው መወያየታቸውን ዋይት ሃውስ አስታውቁዋል። በተከታታይም ገለጻ ይደረግላቸዋል ብሏል፡፡

የአሜሪካየውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊነክን፣ ትንናት በሰጡትመግለጫ ደግመው እንደተናገሩት፣ ዩናይትድ ስቴትስበአፍጋኒስታን ከእስላማዊ ቡድን ደጋፊዎች ሊመጡ የሚችሉ አደጋዎችን አሜሪካ እያየች ነው ማለታቸው ይታወሳል፡፡

XS
SM
MD
LG