በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቤላሩስ ላይ የሚጣለው ማዕቀብ እንዲፋጠን ተጠየቀ


የአውሮፓ መማክርት ፕሬዚዳንት ቻርለስ ሚችል፣ በቤላሩስ ላይ ማዕቀብ የመጣልሉ ሃሳብ እንዲፋጠን ጥሪ አድርገዋል። የተለያዩ የተቃውሞ መሪዎች ከታሰሩ በኋላ ነው ባለሥልጣኑ ጥሪውን ያቀረቡት።

ቤልሩስ ውስጥ በፖለቲካ ምክንያት ስዎችን ማሰርንና በግዴታ ከሀገር ማስወጣትን ያካተቱ የፖለቲካ ወከባዎች መቆም አለባቸው ሲሉ፣ ሚቼል ትላንት በትዊተር ገፃቸው ገልጸዋል። የቤላሩስ ባለሥልጣኖች መላ የፖለቲካ እስረኞችን መፍታት አለባቸው። የዜጎችን የመናገርና የመሰብሰብ መብት ማክበር አላባቸው” በማለትም አክለዋል።

ለረዥም ጊዜ ሥልጣን ላይ በቆዩት አለክሳንደር ሉካሸንኮ ላይ የሚካሄደው ተቃውሞ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት፣ ከእስር ተርፈው ከነበሩት ሁለት የተቃውሞው ካውንስል አባላት አደንኛው፤ ማንነታቸው ባልታወቀ የሀገሪቱ ባለሥልጣኖች መታሰራቸው ታውቋል።

አብረዋቸው የሚሰሩት ግሌብ ጀርመን በተናገሩት መሰረት፣ ጠበቃ ማክሲም ዝናክ ጭምብል ባጠለቁ ሰዎች፣ ከአስተባባሪው ካውንስል መሥርያ ቤት ተወሰደዋል።

XS
SM
MD
LG