በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞ የዋይት ኃውስ ዋና ስትራተጂ አውጭ የነበሩት ስቲቭ ባነን

የቀድሞ የዋይት ኃውስ ዋና ስትራተጂ አውጭ የነበሩት ስቲቭ ባነን
የቀድሞ የዋይት ኃውስ ዋና ስትራተጂ አውጭ የነበሩት ስቲቭ ባነን

የቀድሞ የዋይት ኃውስ ዋና ስትራተጂ አውጭ የነበሩት ስቲቭ ባነን የፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ዋና አማካሪ ስለነበሩበት ወቅት ዛሬ በተወካዮች ምክር ቤት የሥለላ ኮሚቴ በመጥሪያ ቀርበው ቃላቸውን ሊሰጡ ተይዞ የነበረውን ቀጠሮ ይለፈኝ ማለታቸው ተሰማ።

የቀድሞ የዋይት ኃውስ ዋና ስትራተጂ አውጭ የነበሩት ስቲቭ ባነን የፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ዋና አማካሪ ስለነበሩበት ወቅት ዛሬ በተወካዮች ምክር ቤት የሥለላ ኮሚቴ በመጥሪያ ቀርበው ቃላቸውን ሊሰጡ ተይዞ የነበረውን ቀጠሮ ይለፈኝ ማለታቸው ተሰማ።

ባለፈው የፕሬዚደንታዊ ምርጫ የሩስያን ጣልቃ ገብነት በተመለከተ ኮሚቴው የሚያካሂደውን ምርመራ የሚመሩት የቴክሳሱ ሪፖብሊካን ማይክ ካናዌይ ባነን ቀርበው ቃላቸውን ይሰጣሉ ብለው ነበር። ለኮሚቴው ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለዜና ማሰራጫዎች እንደገለጹት ግን ስለሚቀርቡት ጥያቄዎች በኮሚቴውና በዋይት ኃውስ መካከል ካለው አለመግባባት በተያያዘ ባነን ኮሚቴው ዘንድ አይቀርቡም።

ባንነ ተጠርተው ባለመቅረባቸው ኮንግሬስን በመዳፈር ሊከሰሱ ይችላሉ ሆኖም ምክር ቤቱ እርምጃ ይወስድባቸው እንደሆን ለጊዜው ግልፅ አይደለም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG