በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአይቮሪኮስት የእርስ በርስ ጦርነት ለተወነጀሉ በተሰጠ ምህረት ሲሞን ባግቦ ይገኙበታል

Ivory Coast's former first lady Simone Gbagbo (R), who is accused of crimes against humanity and war crimes for her alleged role in a 2011 civil war, arrives in a domestic court in Abidjan, May 31, 2016.

የአይቮሪኮስት ፕሬዚዳንት አላሳን ዋታራ ከሰባት ዓመታት በፊት የብዙ ሰዎች ደም ካፋሰሰው የእርስ በርስ ጦርነት በተያያዙ ጥፋቶች ለተወነጀሉ ሰዎች ትናንት በሰጡት ምህረት ተጠቃሚዎች መካከል አንዷ የቀድሞ የሀገሪቱ ቀዳማዊት እመቤት ሲሞን ባግቦ መሆናቸው ታወቀ።

የአይቮሪኮስት ፕሬዚዳንት አላሳን ዋታራ ከሰባት ዓመታት በፊት የብዙ ሰዎች ደም ካፋሰሰው የእርስ በርስ ጦርነት በተያያዙ ጥፋቶች ለተወነጀሉ ሰዎች ትናንት በሰጡት ምህረት ተጠቃሚዎች መካከል አንዷ የቀድሞ የሀገሪቱ ቀዳማዊት እመቤት ሲሞን ባግቦ መሆናቸው ታወቀ።

ሲሞን ባግቦ በብጥብጡ በተጫወቱት ሚና የሀገር ደኅንነትን አደጋ ላይ በመጣል ወንጀል ተከሰው በሃያ ዓመት እሥራት እንዲቀጡ ተፈርዶባቸው እንደነበር ይታወሳል። ባለፈው ዓመት ደግሞ በሰብዓና ላይ ወንጀል በመፈፀም በተመሰረተባቸው ክስ ከወንጀሉ ነፃ ተብለዋል።

አቃቤ ሕጎች በወቅቱ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሎራን ባግቦ ተቃዋሚዎች ላይ የበቀል ጥቃት የሚፈፅም ቡድን አድራጅተው የጦር መሳሪያና ሄሊኮፕተርም ጭምር እየሰጡ ሲንቀሳቀሱ ነበር ብለው ወንጅለዋቸዋል።

ሎራን ባግቦ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በአላሳን ዋታራ መሸነፋቸውን አልቀበልም ካሉ በኋላ አአአ በ2011 በተቀሰቀሰው ብጥብጥ ቁጥራቸው ወደ ሦስት ሺህ የሚጠጋ ሰዎች ተገድለዋል። ያን ተከትሎ ተይዘው ለሄጉ የዓለምቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት ተሰጥተው በሰብዕና ላይ ወንጀል በመፈፀም ክስ ሂደት ላይ ናቸው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG