በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋና አንድ ሚሊዮን ዶላር ከቤታቸው የተሰረቁት ሚኒስትር ተያዙ


ሲሲሊያ አቤና ዳፓ
ሲሲሊያ አቤና ዳፓ

በጋና፣ አንድ ሚሊዮን ዶላር ጥሬ ገንዘብ፣ በቤት ሠራተኞቻቸው ተሰርቋል፤ መባሉን ተከትሎ በሳምንቱ መጨረሻ ሥልጣናቸውን የለቀቁት ሚኒስትር፣ በሙስና እንደተጠረጠሩና በዛሬው ዕለት በቁጥጥር ሥር እንደዋሉ ታውቋል።

የጽዳት ሚኒስትሩ ሲሲሊያ አቤና ዳፓ፣ ያን ያህል ገንዘብ እንዴት በመኖሪያ ቤታቸው ሊገኝ እንደ ቻለ፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥያቄ አንሥተዋል።

ሙስና እና ከሙስና ጋር የተያያዘ ወንጀል ሳይፈጽሙ አይቀርም በሚል ጥርጣሬ ሚንስትሯ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ልዩ ዐቃቤ ሕጉ አስታውቀዋል።

ሚኒስትሯ የተያዙት፣ የፕሬዚዳንት ናና አኩፎ አዶ መንሥስት፣ አገሪቱ የገጠማትን የኢኮኖሚ ቀውስ ለማስተካከል በሚጥርበትና ከዓለም አቀፉ የገዘብ ተቋም(IMF)፣ ሦስት ቢልዮን ዶላር ብድር በሚሻበት ወቅት ነው።

ከሚኒስትሯ መኝታ ቤት፣ ከአንድ ሚሊዮን ዶላሩ በተጨማሪ፣ 300ሺሕ ዩሮ እና በሚሊዮን የሚቆጠር የአገሪቱን ጥሬ ገንዘብ ወስደዋል፤ የተባሉት የቤት ሠራተኞች፣ የስርቆት ክሥ እንደተመሠረተባቸው፣ የኤኤፍፒ ዘገባ አክሎ አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG