ዋሺንግተን ዲሲ —
የቡሩንዲ አዲስ ፕረዚዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሽሜ በሀገሪቱ መዲና ጊቴጌ በሚገኘው ኢንጎማ ስቴድዮም፣ የፕረዚዳንትነት ቃለ - መሃላ ፈጸሙ። ፕረዚዳንት ፔር ንኩሩንዚዛ በድንገት ካረፉ፣ ሳምንት በሁዋላ ማለት ነው።
ንዳይሽሜ ቃለ - መሃላ እንዲፈጽሙ የታቀደው ባለፈው ነሃሴ ወር የነበረ ሲሆን በንኩሩንዚዛ ሞት ምክንያት ተራዝሟል። ይሁንና ተመራጩ ፕረዚዳንት በተቻለ ፍጥነት ቃለ-መሃላ እንዲፈጽሙ፣ የሀገሪቱ ህገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት፣ ባለፈው ሳምንት ወስኗል።
አዲሱ የቡሩንዲ ፕረዚዳንት ባለፈው ግንቦት ወር በተካሄደው ምርጫ፣ 60 ከመቶ በላይ ድምጽ አግኝታው ማሸነፋቸው የሚታወስ ሲሆን ሥልጣን ላይ የሚቆዩትም ለሰባት ዓመታት ነው።