በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አውሮፓ የሕክምና ድርጅት እያቋቋመች ነው


ጠ/ሚ ኡርሱላ ፎን ዴር ሌየን የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት
ጠ/ሚ ኡርሱላ ፎን ዴር ሌየን የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት

የአውሮፓ መሪዎች የኮሮናቫይረስን ወረርሽኝ ለመዋጋት አንድ ዓለማቀፍ የሕክምና ድርጅት እያቋቋሙ መሆናቸውን አስታወቁ።
በእንግሊዙ ዘ ኢንዲፔንዳንት ጋዜጣ ላይ ፅሁፍ ያወጡት የጣሊያን፣ የጀርመን፣ የፈረንሣይ፣ የስፔን፣ የኖርዌይና የአውሮፓ ህብረት መሪዎች 8 ቢሊዮን ዶላር ለድርጅቱ ማቋቋሚያ እየዋጡ መሆናቸውንና እንዲሁም የዓለም የጤና ድርጅትን እንደሚደግፍ፣ ቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፈወንዴሽንና ዌልካም ትረስትን የመሳሰሉ ተቋማትን ጥረቶች እንደሚቀላቀሉ አስታውቀዋል።
በመላው ዓለም ለአዲሱ ኮሮናቫይረስ የተጋለጠው ሰው ቁጥር 3 ሚሊዮን አራት መቶ የደረሰ ሲሆን ወደ 244 ሺህ ሰው ሞት።
ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ 1.7 ሚሊዮን ሰው መጋለጡንና 67 ሺህ 300 ሰው በኮቪድ-19 መሞቱን ዛሬ የወጡ መረጃዎች ያሳያሉ።

XS
SM
MD
LG