በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢራን የኒውክሊየር ስምምነት


የኢራኑ ፕሬዚዳንት ሃሳን ሩሃኒ
የኢራኑ ፕሬዚዳንት ሃሳን ሩሃኒ

ኢራን የየኒውክሊየር መርሃ ግብሩዋን የሚገድበውን ስምምነት የማክበሩዋን ጉዳይ በተመለከተ ሁሉም ወገኖች በአስቸኳይ ተሰብስበው ኣንዲነጋገሩበት አውሮፓውያኑ የውሉ ፈራሚዎች እየጠየቁ ናቸው።

የተባበሩት መንግሥታት የአቶሚክ ድርጅት ኢራን እኤአ በ2015 በተፈረመው ስምምነት ከተወሰነላት የዳበረ ዩሬንየም መጠን ማለፉዋን ትናንት ካረጋገጠ በኋላ ብሪታንያ ፈረንሳይ ጀርመን እና የአውሮፓ ህብረት በዛሬው ዕለት የአስቸኳይ ስብሰባ ጥሪውን አቅርበዋል።

ኢራን በውሉ የተካተተውን አብዛኛውን የጋራ ድርጊት መርኃ ግብር አለማሟላቷ አስግቶናል ሲሉ አውሮፓውያኑ የውሉ ፈራሚዎች አስታውቀዋል። ኢራን መርኃ ግብሩ ውስጥ መቆየት እንደምትፈልግ አስታውቃቸው እንደነበር የገለጹት የአውሮፓ መሪዎች ሆኖም በዚያ መሰረት አድራጎቷቸዋን በአስቸኳይ ቀልብሳ የድርጊት መርኃ ግብሮቹ በአስቸኳይ ማክበር አለባት ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከፍተኛ ዲፕሎማት ውጥረትን ለማርገብ ሊሞክሩ ለሁለት ቀን ወደቴህራን ተጉዘዋል። ማክሮን እና የኢራኑ ፕሬዚዳንት ሃሳን ሩሃኒ የዩሬንየም ማበልፀጉን ጉዳይ በተመለከተ እኤአ ሃምሌ 15 በፊታችን ሳምንት ሰኞ የጊዜ ገደብ መፍትሄ ለማግኘት መስማማታቸው ይታወሳል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG