ዋሺንግተን ዲሲ —
የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊ ፌዴሪካ ሞግኸርኤኒ የኢራን ኑክሌርን በሚመለከት የተደረገው ዓለምቀፍ ሥምምነት እየሰራ ነው ብለዋል። የኢራን የቦሊስቲክ ሚሳይልና በመካከለኛው ምሥራቅ የሚስተዋሉ ሌሎች እንቅስቃሴዎች አሳሳቢ ቢሆኑም፣ እነዚ በተለየ መልክ የሚታዩ ናቸው ሲሉም አክለዋል።
የውጭ ጉዳይ ኃላፊዋ ይህን ያሉት ከሁለት ዓመታት በፊት ከኢራን ጋር ስለተደረገው ሥምምነት ለመነጋገር ብራሰልስ ውስጥ ከብሪታንያ፣ ከፈረንሳይ፣ ከጀርመንና ከኢራን የውጭ ሚኒስትሮች ጋር ከተገናኙ በኋላ ነው።
ስምምነቱ የኢራንን የኑክሌር ፕሮግራም በመገደብ ተጥሎባት የነበረውን የገንዘብ ማዕቀብን ያቃለለ ነው።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ