የፌስቡክ እናት ኩባንያ ሜታ ‘ማርኬትፕሌስ’ የተሰኘውን የማስታወቂያ አገልግሎት ከማኅበራዊ መገናኛው ፌስቡክ ጋራ አስተሳስሮ በማቅረብ በሌሎች የማስታወቂያ አገልግሎቶች ላይ ፍትሃዊ ያልሆነ ጫና አሳድሯል፣ በዚህም የአውሮፓ ኅብረትን ህግ ጥሷል በሚል የኅብረቱ ኮሚሽን የ840.24 ዶላር መቀጫ እንዲከፍል አዟል።
ሜታ የፌስቡክ ማርኬትፕሌስ ያልተገባ ጥቅም እንዲያገኝ አድርጓል ሲል ኮሚሽኑ አስታውቋል።
ሜታ በበኩሉ ቅጣቱን ይግባኝ እንደሚል አስታውቆ፣ እስከዛው ግን የተጠቀሱትን ችግሮች በተመለከት አስቸኳይ መፍትሄ እንደሚሻና ህጉን በማክበር እንደሚሰራ አስታውቋል።
ፌስቡክ፣ ማርኬትፕሌስ የተሰኘውን የማስታወቂያ አገልግሎት ከማኅበራዊ ሚዲያው ጋራ በማገናኘት ያልተገባ ጥቅም አግኝቷል በሚል ነበር ኩሚሽኑ ከሁለት ዓመታት በፊት ሜታ ላይ ክስ የመሠረተው።
ፌስቡክ ማርኬትፕሌስን የጀመረው በእ.አ.አ 2016 ሲሆን ከአንድ ዓመት በኋላም በበርካታ የአውሮፓ ሃገራት አገልግሎቱን አስፋፍቷል።
ኮሚሽኑ ሜታ የማርኬትፕሌስ አገልግሎትን ለፌስቡክ ተጠቃሚዎች ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ አቅርቧል ሲል፣ ሜታ በበኩሉ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ማርኬትፕሌስን የመጠቀምም ሆነ ያለመጠቀም አማራጭ አላቸው ይላል።
የአውሮፓ ኅብረትን ሕግን የሚጥሱ ኩባንያዎች ከአጠቃላይ ገቢያቸው 10 ከመቶ መቀጫ ይጣልባቸዋል።
መድረክ / ፎረም