በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍልሰተኞች በሊቢያ ጠርፍ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ሁለት የፈረንሳይ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ሰማኒያ አንድ ፍልሰተኞችን ትናንት ዕሁድ ሊቢያ ጠረፍ ላይ ከሜዲትራኒያን ባህር ማውጣታቸው ተገለፀ። ካለፈው ዓርብ ወዲህ ከባህሩ ተደርሶላቸው የተረፉት ፍልሰተኞች ቁጥር 211 ደርሷል።

ድንበር የለሽ ሃኪሞች እና /SOS/ ሜድቴራንያን ናቸው በኖርዊይ ባንዲራ በምትጓዘው ኢሺን ቫይኪንግ በተባለች መርከብ ደርሰው ፍልሰተኞቹ ያወጧቸው።

ባለፉት ሦስት ቀናት ተደርሶላቸው ከባህሩ ሊወጡ የቻሉት አብዛዛኞቹ ሱዳናውያን ወንዶች መሆናቸው ተገልጿል።

በአካባቢው የምንቀሳቀሰው እኛ ብቻ ነን። የሊቢያ የጠረፍ ጥበቃ ለተቸገሩ ፍልሰተኞች ባህሩ ላይ ጭንቅ ላይ ለሚወድቁ ምላሽ እየሰጡ አይደሉም ሲሉ የSOS ሜድቴራንያን ኣንቅስቃሴ አስተባባሪ ገልፀዋል።

የአካባቢው የአየር ሁኔታ አመቺ በመሆኑና በኢድ በዓልም ምክንያት ብዙ የባህር ዳርቻ ጥበቃ ላይ ፖሊሶች በብዛት ስለማይሰማሩ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናትም ተጨማሪ ፍልሰተኞች ከሊቢያ ጠረፍ መንቀሳቀሳቸው አይቀርም ሲሉ ሥጋታቸውን ገልፀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ “ ኦፕን አርምስ” የተባለ የስፔን ግብረ ሰናይ ቡድን በነፍስ አድን መርከቡ ላይ አንድ መቶ ስድሳ ፍልሰተኞች እንዳሉ ገልጾ ሦስቱ ልዩ የህክምና ዕርዳታ የሚይስፈልጋቸው መሆኑን አስታውቁዋል።

የግብረ ሰናይ ድርጅቱ መስራች ኦስካር ካምፕስ ትናንት ዕሁድ ለአውሮፓ መንግሥታት በተለይም በቅርብ ርቀት ወደብ ላላት ለኢጣሊያ መንግሥት ድጋሚ ተማፅኖ አቅርበዋል።

“ በዚህ በነሃሴ ከባድ ሙቀት አስር ቀን ሙጅሉ መርከብ ላይ ናቸው። ጥረታችንን መቀጠል ያለብን በ160 ምክንያት ነው። አንድ መቶ ስድሳ ሰብዓዊ ፍጡራን ይዘናል ደህንነታቸው ትጠብቆ መውረድ መብታቸው ነው። “ የአውሮፓ መንግሥታት ዕፈሩ” ሲሉ በትዊተር ምሬታቸውን አሰምተዋል።

እጅግ የከረረ ቀኝ ክንፍ አቋም አራማጁ የኢጣሊያ የአገር አስተዳደር ሚኒስትር ማቴዎ ሳልቪኒ ሃገራቸው “ ማንነታቸው የማይታወቅ ፍልሰተኞችን የመቀበል ህጋዊ ግዴታም ሆነ ፍላጎት የላትም ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG