ዋሺንግተን ዲሲ —
ኦፕን አርምስ የተባለው እና በዚሁ ስም በሚጠራ ግብረ ሰናይ ድርጅት የሚንቀሳቀስ የፍልሰተኛ ነፍስ አድን መርከብ አንድ መቶ አርባ ሰባት ፍልሰተኞች ጭኖ ለሁለት ሳምንታት ያህል ባህሩ ላይ ሲዋልል ቆይቷል።
ኦፕን አርምስ ባወጣው መግለጫ እንዳለው የኢጣሊያ ዳኛ ዛሬ በሰጡት ውሳኔ የአገር አስተዳደር ማቴዎ ሳልቪኒ መርከቡ ወደባችን ኣንዳይደርስ ብለው የአስተላልፉት ትዕዛዝ ዓለም አቀፍ ህግ የጣሰ ነው ብለውታል፤ ሳልቪኒ ይግባኝ እንደሚሉ አስታውቀዋል ። ነገር ግን በይግባኙ ምክንያት መርከቡ ላምፔዱሳ መቆም እይችል እንደሆን ለጊዜው አልታወቀም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ድንበር የለሽ ሃኪሞች እና ኤስ ኦ ኤስ ሜድቴራንያን የተብሉት ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የሚንቀሳቀሰው ኦሺን ቫይኪንግ የተባለው እና የሚበዙት ሱዳናውያን ወጣቶች የሆኑ ሦስት መቶ ሃምሳ ስድስት ፍልሰተኞችን ያሳፈረው መርከብ ማረፊያ ወደብ እየፈለገ ነው።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ