በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለገዳማይቱ ተፈናቃዮች ድጋፍ ተጠየቀ


ከገዳማይቱ ከተማ የተፈናቀሉ
ከገዳማይቱ ከተማ የተፈናቀሉ

የአፋርና ሶማሌ ክልሎች ከሚወዛገቡባቸው ሦስት ቀበሌዎች አንዷ በሆነችው ገዳማይቱ ወይም ገርበኢሴ ከተማ በነዋሪዎች ላይ እየደረሰ ነው ያለው የህይወት መጥፋት፣ ንብረት መውደምና መፈናቀል እንደሚያሳስበው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ባወጣው መግለጫ የአፋርና ሶማሌ ክልሎች ከሚወዛገቡባቸው ሦስት ቀበሌዎች አንዷ በሆነችው ገዳማይቱ ወይም ገርበኢሴ ከተማ በነዋሪዎች ላይ እየደረሰ ነው ያለው የህይወት መጥፋት፣ ንብረት መውደምና መፈናቀል እንደሚያሳስበው ገልጿል። ኮሚሽኑ በመግለጫው በግጭቱ ምክንያት የሞቱትንና ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ቁጥር እንዲሁም የደረሰውን የንብረት ውድመት መጠን ያለው መረጃ ውስን እንደሆነ ገልጾ ለዚህም የጸጥታው ሁኔታ ወደነበረበት ባለመመለሱ እንደሆነ አስታውቋል።

ጥቃት የደረሰባቸውና የተፈናቀሉ ሰዎችን በስፍራው ተገኝተው የጎበኙት የሶማሌ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ መሀመድ ሮብሌ ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት ቃል የገዳማይቱ ወይም ገርበኢሴ ከተማ በአሁኑ ሰዓት በአፋር ክልል ልዩ ሃይሎች ስር እንደሆነ ገልጸው የተፈናቀሉ ነዋሪዎችም 3ሺ አባወራዎች እንደሚሆኑ ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ለገዳማይቱ ተፈናቃዮች ድጋፍ ተጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:52 0:00


XS
SM
MD
LG